ከባሏ ዳጎስ ያለ ክፍያ ለማግኝት በሚል ልጇን ያገተችው እናት መነጋገሪያ ሆናለች
እናትየዋ ልጇን በማሳገት ባሏ 14 ሺህ ዶላር እንዲከፍል ያቀደችው እቅድ ለእስር ዳርጓታል
ፖሊስ ባደረገው ክትትል የ14 ዓመት እድሜ ያለው ታዳጊ በእናቱ የቅርብ ሰዎች መታገቱን ደርሼበታለሁ ብሏል
ከባሏ ዳጎስ ያለ ክፍያ ለማግኝት በሚል ልጇን ያገተችው እናት መነጋገሪያ ሆናለች።
በደቡብ አሜሪካዊቷ ኮሎምቢያ አንዲት እናት ከ14 ዓመት ልጇ ጋር በመንገዶች ዳር ለመዝናናት የእግር ጉዞ እያደረገች እያለ ነበር ልጇ በሞተር ሳይክል የመጡ ሰዎች ነጥቀው የወሰዱባት።
የድረሱልኝ ጩኸቷን ያሰማችው ይህች ልጇ ፊታቸውን በሸፈኑ ሰዎች እንደተወሰዱባት ለአካባቢው ነዋሪዎች እና ፖሊስ ተናግራለች ተብሏል።
በደቡባዊ ኮሎምቢያ ካሪቤ ቨርዴ ልጁን አግተው ወስደዋል የተባሉት እነዚህ ሰዎችም ልጁን ለማስለቀቅ 14 ሺህ ዶላር እንዲከፍሉ ጠይቀዋል ተብሏል።
የኮሎምቢያ ፖሊስም ባደረገው ማጣራት አጋቾችን በቁጥጥር ስር ማዋሉ ሲገለጽ በተደረገው ማጣራትም ታግቷል የተባለው ታዳጊ በእናቱ አቀነባባሪነት እንደታገቱ ተገልጿል ሲል ብሉምበርግ ዘግቧል።
እናትየው ይህን ለምን እንዳደረገች ስትጠየቅም የልጇ አባት ገንዘብ እንደማይሰጣት እና ተጨማሪ ገንዘብ ለማግኘት ስትል እንዳደረገችው ለፖሊስ ተናግራለች።
ይህች እናት እና ተባባሪዎቿ በፖሊስ ቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆን የዓመታት እስርም እንደሚጠብቃቸው ተገልጿል።