የቦትስዋና ሀገር አቀፍ ምርጫ ውጤት ላይ የቀረበ ቅሬታ ውድቅ ሆነ
የቦትስዋና ከፍተኛ ፍርድ ቤት በሀገሪቱ የተካሄደውን የምርጫ ውጤት ተከትሎ ዋና ከሚባለው የፖለቲካ ተቃዋሚ ፓርቲ የቀረበውን ቅሬታ ውድቅ ማድረጉን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
ባሳለፍነው ጥቅምት ወር በተካሄደው ምርጫ በስልጣን ላይ ያለው የፕሬዝዳንት ሞግዌሲ ማሲሲ ቦትስዋና ዴሞክራቲክ ፓርቲ (ቢዲፒ) 38 የፓርላማ መቀመጫዎችን በማግኘት አሸንፏል፡፡
ተቀናቃኙ አምብሬላ ፎር ቼንጅ ፓርቲ (ዩ ዲ ሲ) ደግሞ 15 ወንበሮችን ማግኘቱ ተነግሯል፡፡
ውጤቱን ያልተቀበለው ዩ ዲ ሲ ፓርቲ ለሀገሪቱ ፍርድ ቤት ባቀረበው ቅሬት በሙስናና ሌሎች የህግ ጥሰቶች ተጨማልቀዋል ብሎ የጠቀሳቸው ግለሰቦች አንዳቸውም የምርጫ አስፈፃሚነት ሚና ያልነበራቸው በመሆኑ ፍርድ ቤቱ ውድቅ አድርጎታል፡፡
ቦትስዋና 1966 ከብሪታንያ ነፃ ከወጣች ጀምሮ ሀገሪቱን እየመራ ያለው አሁን በስልጣን ላይ ያለው ቢዲ ፓርቲ ነው፡፡
ሀገሪቱ ከፍተኛ የአልማዝ ክምችት ያለባት በመሆኗ የተረጋጋችና ምጣኔ ሀብቷም የተሻለ መሆኑን ቢቢሲ ዘግቧል::