የአውሮፓ ህብረት ለኢትዮጵያ ተጨማሪ 22 ሚሊዮን ዩሮ እርዳታ ሰጠ
ህብረቱ በተያዘው ዓመት በአጠቃላይ ለኢትዮጵያ አምስት ቢሊዮን ብር ገደማ ድጋፍ አድርጓል
የገንዘብ ድጋፉ በግጭት እና ድርቅ ለተጎዱ ሰዎች ድጋፍ ይውላል ተብሏል
የአውሮፓ ህብረት ለኢትዮጵያ ተጨማሪ 22 ሚሊዮን ዩሮ እርዳታ ሰጠ፡፡
የአውሮፓ ህብረት ለአልዐይን በላከው መግለጫ እንዳስታወቀው ተጨማሪ 22 ሚሊዮን የሮ ወይም ከ1 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር ድጋፍ ማድረጉን አስታውቋል፡፡
ህብረቱ በመግለጫው እንዳለው ከዚህ በፊት ለኢትዮጵያ ለሰብዓው ድጋፎች የሚውል 60 ሚሊዮን ዩሮ ወይም 3 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር መስጠቱን ገልጿል፡፡
ኢትዮጵያ የአውሮፓ ህብረት በህዳሴው ግድብ ዙሪያ ያወጣውን መግለጫ ውድቅ አደረገች
ህብረቱ አሁን ከለገሰው 22 ሚሊዮን ዩሮ ጋር በተያዘው የፈረንጆቹ 2023 ዓመት ውስጥ በአጠቃላይ ለኢትዮጵያ የረዳው ገንዘብ መጠን 4 ነጥብ 8 ቢሊዮን ብር ይደርሳልም ብሏል፡፡
በኢትዮያ ባለፉት ዓመታት የነበረው ጦርነት፣ ድርቅ እና መፈናቀል ምክንያቶች የሰብዓዊ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው ዜጎች ቁጥር ከፍ ማለቱ እርዳታ ለማድረግ እንዳነሳሳውም አስታውቋል፡፡
ከዚህ በተጨማሪም በሶማሊያ በግጭት ምክንያት የተሻለ ደህንነት ፍለጋ ወደ ኢትዮጵያ የገቡ ዜጎችን ቁጥር 890 ሺህ ከፍ አድርጎታል ብሏል፡፡
በህብረቱ የቀውስ አስተዳድር ኮሚሽነር ጃኔዝ ሊናርሲስ እንዳሉት “ በኢትዮጵያ የሰብዓዊ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው ዜጎች ቁጥር መጨመሩ ተጨማሪ ድጋፍ ለማድረግ ተወስኗል” ብለዋል፡፡
“በኢትዮጵያ ያለውን የሰብዓዊ ባለሙያዎቻችን ሁኔታዎችን እየተከታተሉ ነው” ያሉት ኮሚሽነሯ ድጋፍ ከሚያስፈልጋቸው ዜጎች ጎን መሆናቸውንም አክለዋል፡፡