የካቶሊካውያኑ አባት የሰላም ጥሪ ለኢትዮጵያ ግብጽ እና ሱዳን
አባ ፍራንቸስኮስ ለተወደደው ህዝባችሁ እና ለመላው ዓለም ስትሉ “ውይይት ብቻ ምርጫችሁ ይሁን” ብለዋል
የዓለም ካቶሊካውያን አባት ግድቡን በተመለከተ ተጀመረው ውይይት እንዲቀጥል ጥሪ አቀረቡ
የዓለም ካቶሊካውያን አባት ግድቡን በተመለከተ ተጀመረው ውይይት እንዲቀጥል ጥሪ አቀረቡ
ኢትዮጵያ፣ሱዳንና ግብጽ ግድቡን በተመለከተ የጀመሩትን ውይይት አጠናክረው እንዲቀጥሉ የዓለም ካቶሊካውያን አባት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ጥሪ አቀረቡ፡፡
አባ ፍራንቸስኮስ ግድቡን በተመለከተ ያለው ልዩነት ወደ ግጭት እንዳያመራ ጥንቃቄ ሊያደርጉ እንደሚገባም ሃገራቱን አሳስበዋል፡፡
“ዘላለማዊው ወንዝ የህይወት ምንጭ፣ የሚያለያይ ሳይሆን የሚያቀራርብ፣ ከጠላትነት ይልቅ ወዳጅነትን፣ብልጽግናን፣ ወንድማማችነትን የሚያጠናክር እንጂ የሚከፋፍል እና ያለመግባባትና የግጭት ምንጭ እንዳይሆን የሚመለከታቸውን ሁሉንም አካላት በጀመሩት የውይይት መንገድ እንዲቀጥሉ ጥሪ አቀርባለሁ” ሲሉም ነው ጥሪያቸውን ያቀረቡት፡
ለተወደደው ህዝባችሁ እና ለመላው ዓለም ስትሉ “ውይይት ብቻ ምርጫችሁ ይሁን”ም ብለዋል አባ ፍራንቸስኮስ ፡፡
ኢትዮጵያ ከሱዳን በምትዋሰንብት ድንበር አቅራቢያ በ15 ኪሎ ሜትሮች ቅርብ ርቀት ላይ የምትገነባው ግዙፍ ግድብ ሶስቱን ሃገራት ማነጋገር ከጀመረ ሰነባብቷል፡፡
ግድቡን የተመለከተው የድርድር ሂደት ሊጠናቀቅ ባለመቻሉም በአፍሪካ ህብረት ስር በመደራደር ላይ ይገኛሉ፡፡
ሆኖም ድርድሩ ሱዳን እና ግብጽ እንዲራዘም ባቀረቡት ጥያቄ ምክንያት ያለፉትን ሳምንታት ሳይካሄድ ቀርቷል፡፡
በመጪው ሰኞ ነሃሴ 11 ቀን 2012 ዓ/ም እንደሚቀጥልም ይጠበቃል፡፡
የግድቡን የመጀመሪያ ዙር ሙሌት በስኬት ያጠናቀቀችው ኢትዮጵያ ለድርድሩ የሚሆን የራሷን የሙሌት ደንብ ማቅረቧ የሚታወስ ነው፡፡