ቁርጥ ጋዳፊን እሚመስለው ሰው የቀድሞው ፕሬዝዳንት ከየት ተገኙ አስብሏል
የቀድሞው የሊቢያዊያን ፕሬዝዳንት አምሳያ ጋዳፊን ለሚናፍቁ የሀገሪቱ ዜጎችን ትኩረት ስቧል
ግለሰቡ ወደ አደባባይ ብቅ ያለበት ወቅት መሀመድ ጋዳፊ በመሩት የሊቢያ አብዮት 54ኛ ዓመት ጋር መደራረቡ ግርምትን አጭሯል
ቁርጥ ጋዳፊን እሚመስለው ሰው የቀድሞው ፕሬዝዳንት ከየት ተገኙ አስብሏል።
ሙዓሙር ጋዳፊ በፈረንጆቹ 1969 በተካሄደው የሊቢያ አብዮትን በመምራት የሊቢያዊያንን ፖለቲካ የቀየሩ ሰው ናቸው።
እኝህ ታሪካዊ የአፍሪካ ፖለቲከኛ ከተገደሉበት 2011 ድረስ ሊቢያ የተረጋጋች፣ ሀብታም እና ተጽዕኖ ፈጣሪ ሀገርም ነበረች።
የቀድሞው ፕሬዝዳንት መዓመር ጋዳፊ ሊቢያዊያን ባስነሱት ተቃውሞ እና በምዕራባዊያን እርዳታ በአዛዛኝ መልኩ ከተገደሉ በኋላ ሰላም የራቃት፣ የሽብርታኞች እና የህገ ወጥ ሰዎች ዝውውር ወንጀል ማዕከል ሆናለች።
በጎበዝ አለቃ እየታመሰች ያለችው ሰሜን አፍሪካዊቷ ሀገር ሊቢያ ዜጎቿ በሀገራቸው ሁኔታ በሀዘን ላይ ባሉበት አንድ ሰው ቁርጥ ጋዳፊን መሳይ ሰው ተከስቷል።
ይህ ግለሰብ በአለባበሱ፣ አካላዊ ሁኔታዊ እና በሌሎች ድርጊቶቹ ሁሉ ቁርጥ የቀድሞ ፕሬዝዳንት ጋዳፊን መምሰሉ የብዙ የሀገሬውን ሰው ትኩረት ስቧል።
ሊቢያ በተቸገረችበት ወቅት ድንገት ደርሶ የሚታደግ ፖለቲከኛ በተናፈቀበት በአሁኑ ወቅት ይህ የጋዳፊ አምሳያ ሰው መታየት ያዩት እውነት እንዲሆን በመመኘት ላይ ናቸው ተብሏል።
የጋዳፊ አድናቂ ነው የተባለው ይህ ግለሰብ በሚዘዋወርባቸው ስፍራዎች ሁሉ ሊቢያዊያን እየቀረቡ እያቀፉት እና እየሳሙት እንደሆነ ተገልጿል።
ጋዳፊን መሳዩ ግለሰብም ከሰዎች ጋር ፎቶ እንደሚነሳ የጋዳፊን ስምንም በማንሳት እንደ ሚያመሰግኑት በዘገባው ላይ ተጠቅሷል።
ግለሰቡ ከቀድሞው የሊቢያ ፕሬዝዳንት ጋዳፊ ልጅ ሰይፍ አል ኢስላም ልጅ ጋር የተነሳውን ፎቶም ለሚቀርቡት ሰዎች አሳይቷል ተብሏል።