ዳርኔላ ፍረይዘር የቀረፀችው ቪዲዮ በዓለም አቀፍ ደረጃ የዘር ግድያን ለሚቃወሙ በርካታ ሰልፎች ምክንያት ሆኖ ነበር
የጆርጅ ፍሎይድ ግድያ ስእል የሳለች የ18 ዓመቷ ዳርኔላ ፍረይዘር የጋዜጠኝነት ሽልማት ተሸለመች፡፡
ሽልማቱ የሰጠው በጋዜጠኝነትና አርት ዘርፍ ከፍተኛ ብቃት ላሳዩ ሰዎች “የጋዜጠኝነት ሽልማት የሚያበረክተው” የፑልትዘር ኮሚቴ ነው፡፡
ዳርኔላ ፍረይዘር የጆርጅ ፍሎይድን ግድያን በተመለከተ የቀረፀችው ምስል በዓለም አቀፍ ደረጃ የዘር ግድያን የሚያወግዙ በርካታ የተቃውሞ ሰልፎች እንዲደረጉ ምክንያት ከመሆኑ በዘለለ፤ መርማሪ ፖሊሶች ድርጊቱን በፈጸመው ፖሊስ ድሬክ ቻውቪን ላይ ላቀረቡት ማስረጃ ትልቅ ሚና ተጫውተዋል፡፡
ኮሚቴው "ዳርኔላ ፍረይዘርን የሸለምናት የጆርጅ ፍሎይድ ግድያን የሚሳይ ምስል (ቪድዮ) በመቅረፅዋ ነው፤ ይህ ቪድያ በመላው ዓለም ፖሊሱን በመቃወም ሰልፎች እንዲደረጉ ያስቻለና የጋዜጠንነት ሚናን አጉልቶ ያሳየ ነው" በማለት ወጣቷ የፈፀመችውን ተግባር አወድሷል።
ፍረይዘር ባለፈው አመት ግንቦት 25 በሚንያ ፖሊስ ከአጎቷ ልጅ የእግር ጉዞ በማድረግ ላይ ሳለች ነበር ፍሎይድ በፖሊስ ሲታሰር የተመለከተችው፡፡
"አንድ ሰው በፍራቻ ውሥጥ ሆኖ ፡ ስለ ህይወቱ ሲለምን ተመለከትኩኝ " በማለት ድረጊቱን በሞባይልዋ ለመቅረፅ እንደጀመረች በወቅቱ ለፍርድ ቤት በሰጠችው ቃል መግለፅዋ የሚታወስ ነው፡፡
ለፍድርድ ቤቱ በሰጠችው ቃል ጆርጅ ፍሎይድ 'መተንፈስ አልቻልኩም ' ሲል ነበር፤ ፈርቶ ስለነበርም እናቱን ሲጠራ ነበር ማለቷም እንዲሁ፡፡
ዳርኔላ ፍሬይዘር ምርመራ በተካሄደበት ወቅትም የጆርጅ ፍሎይድ ግድያ ህይወትዋ እንደቀየረው ገልፃ ነበር፡፡
"ጆርጅ ፍሎይድን ሳይ ፡ አባቴን አሰብኩ፣ ወንድሜን ነበር ያሰብኩት፣ የአጎቴ ልጆች፣ አጎቶቼ፤ ምክንያቱም ጥቁር ስለሆኑ ፤ እናም አንዳቸው ላይ እንደተፈፀመ ነበር ያሰብኩት" በማለት በእንባ ታጥባ የሰጠቸው ቃልም ይታወሳል፡፡
የፍሎይድ ግድያ ዓለምን አምጋግሯል፡፡ የተካሄድ የተቃውሞ ሰልፎች በነጮች ላይ ያተኮሩ ሳይሆኑ ፖሊሱ ለፈፀመው ድረጊት ላይ ያነጣጠሩ ናቸው፡፡