ከሞት በስተቀር የማያድነው የለም የሚባለው የጃፓኖች ባህላዊ ህክምና
ሽራካዋ የተሰኘው የጃፓን አኩፐንክቸር ህክምና መጥፎ መንፈሶችን ጨምሮ ብዙ ህመሞችን እንደሚፈውስ ይታመናል
በጃፓን ከ120 ሺህ በላይ የዚህ ባህላዊ ህክምና ባለሙያዎች አሉ
ከሞት በስተቀር የማያድነው የለም የሚባለው የጃፓኖች ባህላዊ ህክምና
የሩቅ ምስራቋ ጃፓን ባህላዊ ህክምና ከሚተገበርባቸው የዓለማችን ሀገራት መካከል አንዷ ናት፡፡
በእስያ በእንግሊዘኛ ቃሉ አኩፐንክቸር የሚባል ባህላዊ ህክምና ያለ ሲሆን ጃፓን ደግሞ ሽራካዋ የተሰኘ የአኩፐንክቸር ህክምና አላት፡፡
ታዋቂ እና ዝነኛ ጃፓናዊናንን ጨምሮ በርካታ የሀገሬው ዜጋ ይጠቀመዋል የሚባለው ይህ ባህላዊ ህክምና በርካታ መርፌዎችን በሰውነት አካል ላይ በመሰካት የሚከወን የህክምና አይነት ነው፡፡
ይህ ሕክምና የጡንቻ መዛል፣ መጥፎ እድል፣ ለውሳኔ መቸገር እና የአዕምሮ ንቃትን ያሻሽላል ተብሎ በሀገሬው ዜጋ ይታመናል ተብሏል፡፡
በተለይም በጃፓን ዋና ከተማ ቶኪዮ ዝነኛ የሆነው ሽራካዋ አኩፐንክቸር ክሊኒክ ህክምና የሚከታተሉ ዝነኛ ጃፓናዊን ፎቶ በማህበራዊ ትስስር ገጾቻቸው ላይ አጋርተዋል፡፡
የክሊኒኩ መስራች ዩሳኩ ሽራካዋ እንዳሉት ህክመናዬን የሚከታተሉ ሰዎች ያለቅሳሉ ህክምናው ነፍስን የማደስ ነው ማለታቸውን ኦዲቲ ሴንትራል ዘግቧል፡፡
ህክምናው በታካሚዎች ላይ መርፌዎቹ ሲሰኩ ህመም ቢፈጥሩም ጽኑ የሆኑ የጡንቻ እና ነርቭ ህመሞችን ማከም ያስችላል ተብሏል፡፡
በጃፓን ሽራካዋ የተባለው አኩፐንክቸር ህክምና ውስጥ አንዱ ሲሆን ከ500 በላይ ሌሎች መሰል ባህላዊ ህክምናዎች በጃፓን ይሰጣሉ፡፡
ሀገሪቱ በአጠቃላይ 120 ሺህ የአኩፐንክቸር ባህላዊ ህክምና ባለሙያዎች እንዳሉ በዘገባው ላይ ተጠቅሷል፡፡