በጃፓን የአዋቂ ዳይፐር ገበያ መድራቱ ተገለጸ
ዳይፐር አምራች ኩባንያዎች ከህጻናት ይልቅ የአዋቂ ዳይፐር መምረት ላይ ተጠምደዋል ተብሏል
የጃፓን ዓመታዊ ዳይፐር ወጪ 612 ሚሊዮን እንደደረሰ ተገልጿል
በጃፓን የአዋቂ ዳይፐር ገበያ መድራቱ ተገለጸ።
በሩቅ ምስራቋ ጃፓን የህዝብ ቁጥር በየጊዜው እያሽቆለቆለ ሲሆን በዛው ልክ የአዛውንቶች ቁጥር ደግሞ እየጨመረ ይገኛል።
አዲስ የሚወለዱ ህጻናት ቁጥር እየቀነሰ መምጣቱ የንጽህና መጠበቂያ ወይም ዳይፐር የሚያመርቱ ኩባንያዎች ትኩረታቸው የአዋቂ ዳይፐር ወደ ማምረት እየዞሩ ናቸው ሲል ሮይተርስ ዘግቧል።
እንደ ዘገባው ከሆነ በጃፓን የአዋቂ ዳይፐር ለህጻናት ተብለው ከሚመረቱ ዳይፐር መጠን ጋር ሲነጻጸር በእጥፍ ይበልጣል።
በጃፓን ለዳይፐር ምርት ተብሎ የሚወጣ ገንዘብ 612 ሚሊዮን ዶላር እንደደረሰ ተገልጿል።
በሀገሪቱ በየዓመቱ የሚወለዱት ህጻናት ቁጥር በዚሁ ከቀጠለ በ2070 የጃፓን ህዝብ ብዛት በ30 በመቶ እንደሚቀንስ ይጠበቃል።
አሁን ላይ 122 ሚሊዮን ህዝብ ብዛት ያላት ጃፓን 30 በመቶ ያህሉ እድሜው ከ65 ዓመት በላይ ነው።
ሀገሪቱ እየቀነሰ የመጣው አዲስ የሚወለዱ ህጻናት ቁጥርን ለመጨመር የተለያዩ ማበረታቻዎችን ዘርግታለች።
የቶኪዮ ከንቲባ ጽህፈት ቤት ከአንድ ወር በፊት ዜጎች በቀላሉ የትዳር አጋር እንዲያገኙ የሚያቀላጥፍ መተግበሪያ ይፋ ማድረጉ ይታወሳል።