ሰራተኞችን ለማማለል ከደመወዝ በተጨማሪ አልኮል እና እረፍት የሚሰጠው ኩባንያ
ኩባንያው አልኮል የጠጡ ሰራተኞች ህመም (ሀንጎቨር) ከተሰማቸው እረፍት ይሰጣልም ተብሏል
![](https://cdn.al-ain.com/images/2025/2/08/258-122411-whatsapp-image-2025-02-08-at-11.22.12-am_700x400.jpeg)
ድርጅቱ ይህን አገልግሎት የሚቀርበው አቅም ያላቸው ኩባንያዎችን ለመቋቋም እንደሆነ ገልጿል
ሰራተኞችን ለማማለል ከደመወዝ በተጨማሪ አልኮል እና እረፍት የሚሰጠው ኩባንያ
በጃፓን በተለያዩ የስራ መስኮች የተሰማሩ ኩባንያዎች እርስ በርስ ከፍተኛ ፉክክር በማድረግ ላይ ናቸው፡፡ በተለይም በመካከለኛ እና ጀማሪ ደረጃ ላይ ያሉ ኩባንያዎች ረጅም ዓመት በሰሩ እና ልምድ ባላቸው የንግድ ተቋማት ተጽዕኖ አለባቸው፡፡
በነዚህ ተጽዕኖዎች ምክንያትም ልዩ ተሰጥኦዎች ያላቸውን ሰራተኞች ለማግኘት እና በስራ ላይ ለማቆየት የሚቸገሩ ሲሆን ከሰሞኑ አንድ የጃፓን ኩባንያ ለሰራተኞቹ ያቀረበው ማትጊያ አግራሞትን ፈጥሯል፡፡
ትረስት ሪንግ የተሰኘው የቴክኖሎጂ ኩባንያ በጃፓኗ ኦሳካ ከተማ መሰረቱን ያደረገ ሲሆን ሰራተኞቹ እንዳይለቁበት እና ልዩ ታለንት ያላቸው አዲ ተመራቂዎችን ለመሳብ በሚል ከደመወዝ ባለፈ ለየት ያለ ማትጊያ ማቅረቡን ገልጿል፡፡
ድርጅቱ የተለያዩ የአልኮል መጠጦችን ለሰራተኞቹ በነጻ ያቀረበ ሲሆን አልኮል ጠጥተው ድካም እና ሀንጎቨር ያስቸገራቸው ሰራተኞች እረፍት ማግኘት እንዲችሉ ፈቅዷል፡፡
ከዚህ በተጨማሪም ሰራተኞች ከቻሉ በቀን ውስጥ እስከ 22 ሰዓት ድረስ መስራት እንደሚችሉ እና የትርፍ ሰዓት ክፍያ እንደሚከፍልም አስታውቋል፡፡
ሰራተኞች በስራ መሀል አልኮል ጎምጨት ማለት ከፈለጉ በነጻ ይቀርብላቸዋል የተባለ ሲሆን ይህም ሰራተኞችን የበለጠ ሀላፊነት እንዲሰማቸው እና በስራቸው ፍሬያማ እንዲሆኑ ሊያግዛቸው ይችላል በሚል አገልግሎቱ እንደቀረበ ኩባንያው አስታውቋል፡፡
የድርጅቱ ስራ አስኪያጅ እንዳሉት ለሰራተኞቻቸው ይህን አቅርቦት ያዘጋጁት አቅም ያላቸው ግዙግ ኩባንያዎች ተጽዕኖዎችን ለመቋቋም እንደሆነ ተናግረዋል፡፡
ድርጅታቸውን ትርፋማ ለማድረግ ለሰራተኞች ከገንዘብ ሌላ አማራጭ ለማቅረብ እንደወሰኑ እና ሰራተኞቻቸውም በዚህ ደስተኞች እንደሆኑ ስራ አስኪያጁ አክለዋል፡፡