![](https://cdn.al-ain.com/images/2025/2/13/258-112730-173-204910-awidow-eats-last-dish-prepared-husband-death-700x400_700x400.jpg)
ሚስትየው በባሏ የተሰራውን ምግብ ትዝታውን ላለማጣት ስትል ለሁለት ዓመት በማቀዝቀዣ ክፍል አቆይተዋለች
በባሏ የተሰራውን ምግብ ለሁለት ዓመት ያስቀመጠችው ሚስት
ሳብሪና ቻይ በጃፓኗ ቶኪዮ ከባሏ ቶኒ ሶንግ ጋር ተጋብተው ይኖሩ ነበር።
ባል ቶኒ ምግብ መስራት አብዝቶ የሚወደው ሙያ ሲሆን ባለቤቱ ሳብሪና ደግሞ ባሏ የሚሰራላትን ምግብ እንደምትወደው ተናግራለች።
እነዚህ ባልና ሚስቶች ከሁለት ዓመት በፊት እንደተለመደው ፍቅራቸው እክል ይገጥመዋል።
ባል ቶኒ ቤት ውስጥ እያለ ባጋጠመው ድንገተኛ የልብ ህመም ምክንያት ህይወቱ ያልፋል።
በተፈጠረው ክስተት ድንጋጤ ውስጥ የነበረችው ሚስት ሳብሪና በባሏ የተሰሩ ምግቦችን ወደ ማቀዝቀዣ ክፍል ውስጥ ታስገባቸዋለች።
ባሏን በማጣቷ እንደተጎዳች የምትናገረው ሚስት ሳብሪና የባሏን ትዝታ ላለማጣት ምግቡን ለማስቀመጥ ትወስናለች።
ህይወት ትዝታ እና ሀዘን ብቻ አይደለም የምትለው ሳብሪና ከሁለት ዓመት በኋላ በባሏ የተሰራውን ምግብ የመጨረሻ ክፍል እያለቀሰች ስትመገብ የሚያሳየው ተንቀሳቃሽ ምስል ብዙ ተመልካች አግኝቷል።
ሳብሪና በባሏ ከተሰሩ ምግቦች ውስጥ የመጨረሻውን ከተመገበች በኋላ አዲስ ህይወት እንደምትቀጥልም ተናግራለች።
ከቶኪዮ ወደ ኒዮርክ ለመዛወር መወሰኗን የተናገረችው ሳብሪና በአዲሱ ሀገር አዲስ ህይወት እና ፍቅር እንደሚገጥማት ተመኝታለች።
መጭው እና አዲሱ ህይወቴ ከፍርሀት የጸዳ እንዲሆን እፈልጋለሁ የምትለው ሳብሪና መጪዎቹን ጊዜ በአዲስ መንፈስ ለመቀበል ዝግጁ መሆኗንም ተናግራለች።