ተመድ በፈረንጆቹ 2021፣ 56 ሀገራትን የሚሸፍኑ 34 የአብአዊ ድጋፍ እቅዶች ማዘጋጀቱን ገልጿል
ተመድ በፈረንጆቹ 2021፣ 56 ሀገራትን የሚሸፍኑ 34 የአብአዊ ድጋፍ እቅዶች ማዘጋጀቱን ገልጿል
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተመድ) የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ በአለም አቀፍ ደረጃ የኮሮና ቫይረስ ተረጅዎችን ቁጥር 40 በመቶ እንዲጨምር እንዳደረገውና በግርድፉ 35 ቢሊዮን ዶላር ለተጎጅዎች እንደሚያስፈልግ አስታውቋል፡፡
የተመድ እርዳታ ሃላፊ ማርክ ሎውኮክ እንተናገሩት እርዳታ የሚፈልጉት ሰዎች በአንድ ሀገር ይገኛሉ ተብሎ ቢታሰብ ከአለም አምስተኛ ትልቅ ሀገር መሆን ይችላሉ፡፡ ወረርሽኙ በደካማ ሀገሮች ላይ ከፍተኛ ጉዳት ማስከተሉንም ገልጸዋል፡፡
ተመድ ለፈረንጆቹ 2021፣ 56 ሀገራትን የሚሸፍኑ 34 የሰብአዊ ድጋፍ እቅዶች ያዘጋጀ ሲሆን ለአለም አቀፍ ደረጃ ለርሃብ ተጋላጭ ናቸው ካላቸው 235 ሚሊዮን ሰዎች መካከል 160 ሚሊዮን የሚሆኑትን ለመርዳት አልሟል፡፡
ኃላፊው ሎውኮክ “ተመድ እርዳታ ከሚፈልጉት 2/3 ሶስተኛው ነው ለመርዳት የምንሞክረው ምክንያቱም፤ ሌሎች እንደቀይመስቀል ያሉት የቀረውን ክፍተት ይሸፍናሉ” ብለዋል፡፡
ለጋሽ ድርጅቶች ለአብአዊ እርዳት 17 ቢሊዮን ዶላር መበስጠት ከፍተኛ የሚባል ድጋፍ አድርደዋል፤ እርዳታው ለመድረስ የታሰቡትን 70 በመቶ መድረስ ተችሏል ብለዋል ሎውኮክ፡፡ ኃላፊው እንደገለጹት በየመን፣በአፍጋኒስታን፣በሰሜን ምስራቅ ናይጀሪያ፣በደቡብ ሱዳን፣ በኮንጎና በቡርኮና ፋሶ ሊከሰቱ የሚችሉ ርሃቦች እንደሚያሳስባቸው ገልጸዋል፡፡