ዩኤኢ በሸህ ዛይድ ቢን ሱልጣን አልነሃያን አመራር ስር ሆና የተመሰረተችበትን 49ኛ አመት አከበረች
ዩኤኢ በሸህ ዛይድ ቢን ሱልጣን አልነሃያን አመራር ስር ሆና የተመሰረተችበትን 49ኛ አመት አከበረች
የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ (ዩኤኢ) በሸህ ዛይድ ቢን ሱልጣን አልነሃያን አመራር ስር ሆና የተመሰረተችበትን 49ኛ አመት በዛሬው እለት አክብራለች፡፡
ዩኤኢ የተመሰረተችበትን ብሄራዊ በዓል ስታከበር ብዙ ስኬቶችን ለማስመዝገብና ሰላም፣ መቻቻል፣መረጋጋት እንዲሁም ብልጽግና በአረቡ አለምና በዓለም ለማስፈን እንደምትሰራ ገልጻለች፡፡
የዩኤኢ ፕሬዘዳንት የሆኑት ሸህ ከሊፋ ቢን ዛይድ አልነሃያን እንዳረጋገጡት መጭው ጊዜ በተስፋና በትክክለኛው መንገድ ለማስኬድ ታቅዷል፡፡የፌደራል መንግስት የተመሰረተበትን 49ኛ አመት እያከበሩ መሆናቸውን ሸህ ቢን ዛይድ ገልጸዋል፡፡
ሸህ ዛይድ የአንድነት መንግስት የተመሰረተበትን ክበረ በአል አስመልክተው “መስከረም ሁለት ማለት ለእኛ-ለህዝቡና ለአመራሩ ለሀገራችን ያለንን ፍቅር የምናጠናክርበት፣ በህዝቡና በአመራሩ መካከል ያለውን ግንኙነት የምናጠናክርበት” ነው ብለዋል፡፡
“የምኮራባትን ሀገር የመሰረቱ የተከበሩ መስራቾችናጠብቀው ያቆዩንን እናከብራለን፤ አንድነቱ የሀገሪቱ ዋና ህይወትና የወደፊት መሻትና የአብሮነት ምልክት ነው”
ሸህ ዛይድ እንደገለጹት መጭው ጊዜ ግልጽ እቅድ፣ ቀድሞ ችግሮችንና መልካም አጋጣሚዎችን መጠበቅን ይጠይቃል፤ የሀገሪቱን በሚቀጥሉት 50 አመታት የምትሰራቸውን ፕሮጀክቶችን ለማዘጀት ውሳኔ የማሳለፍ ወኔ ይጠይቃልም ብለዋል፡፡
የሚኒስቴር መስሪያ ቤቶችን ለመቀየር ፣ ሌሎችንና አዲሶችን ለመፍጠርና አንዳንዶቹን ደግሞ ለማጣመር ውሳኔ መተላፉንም ሸህ ዛይድ አልነሃያን አስታውቀዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ሸህ ቢን ዛይድ አልነሃያን ዩኤኢ የሳይንቲስቶች ምክርቤት፣ የወጣቶች ምክርቤትና እንዲሁም የትምህርትና የሰውሀብት ጠቅላይ ምክርቤት መቋቁሙን በስኬትነት ጠቅሰዋል፡፡
ዩኤኢ ወደ ማርስ ብሮብ ኦፍ ሆፕ የተባለች መንኮራኩር በማምጠቅ ከአረቡ አለም ቀዳሚ መሆኗ ይታወሳል፡፡