ፌደራል ፖሊስ ብሄርን ከብሄር ያጋጭ ነበር ያለውን የ“ድምጸ ወያነ”ቴሌቪዥን ስቱዲዮ መቆጣጠሩን ገለጸ
ፌደራል ፖሊስ ብሄርን ከብሄር ያጋጭ ነበር ያለውን የ“ድምጸ ወያነ”ቴሌቪዥን ስቱዲዮ መቆጣጠሩን ገለጸ
የመከላከያ ሰራዊትና የፌደራል ፖሊስ በትብብር የ “ድምጸ ወያነ”ቴሌቪዥን የመቀሌ ስቱዲዮ መቆጣጠራቸው የፌደራል ፖሊስ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል፡፡
መግለጫው “ድምጸ ወያኔ ቴሌቪዥንና ሬዲዮ ጣቢያዎች የህወሓት ጽንፈኛው ቡድን መሳሪያ በመሆን የሀገርና የህዝብ ህልውና አደጋ ላይ የሚጥሉ፣ብሔርን ከብሔር የሚያጋጩ መረጃዎች በስፋት የሚሰራጩበት ሁኔታ ተስተውሏል” ብሏል፡፡ “የህወሓት ጥንፈኛ ቡድን” የጣቢያውን በርካታ ቁሳቁሶች ማውደሙንም ፖሊስ በመግለጫው አስታውቋል፡፡
በፌደራል መንግስትና በትግራይ ክልል መካከል ያለው አለምግባባት ወደ ግጭት ያመራው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ጥቅምት 24 ህወሓት በክልሉ በሚገኙት የመከላከያ ሰራዊት አባላት ላይ ጥቃት መሰንዘሩንና በህወሓት ላይ እርምጃ እንደሚወሰድ ከሳወቁ በኋላ ነው፡፡
በፌደራል መንግስትና በህወሓት መካከል ያለው አለመግባባት ጨምሮ የነበረው ህወሓት የፌደራል መንግስት “እንደልተካሄደ ይቆጠራል” ያለውን ክልላዊ ምርጫ ባለፈው አመት በማካሄዱ ነው፡፡
ግጭቱ ከተመጀመረ በኋላ ህወሓት ለመደራደር ፍላጎት ቢያሳይም የፌደራል መንግስት ህወገወጦች ወደ ህግ ሳይቀርቡ ድርድር እንዳማይኖር በተደጋጋሚ ማስታወቁ ይታወሳል፡፡ አሁን ላይ መንግስት የትግራይ ክልል ዋና ከተማ የሆነችውን መቀሌን መቆጠጠሩንና የህግ ማስከበር ዘመቻው መጠናቀቁንም አስታውቋል፡፡
መከላከያ አሁን ላይ የቀድሞ የፌደሬሽን ምክርቤት ፕሬዘዳንት ና የህወሓት አባል የሆኑትን የተያዘች ሲሆን ሉሎች የህወሓት ከፍተኛ አመራሮችን በማደን ላይ ነው፡፡