ልዩልዩ
ሉፍታንዛ በአንድ መንገደኛ ላፕቶፕ ኮምፒውተር ላይ ባጋጠመ እክል ምክንያት ለማረፍ ተገዷል
የጀርመኑ ሉፍታንዛ አየር መንገድ ከአሜሪካዋ ሎስአንጀለስ ወደ ፍራንክፈርት በመብረር ላይ ነበር
በመንገደኛው ኮምፒውተር ላይ እሳት መነሳቱን ተከትሎ ነው አውሮፕላኑ ቺካጎ አውሮፕላን ማረፊያ ለማረፍ የተገደደው
ሉፍታንዛ አየር መንገድ በአንድ መንገደኛ ላፕቶፕ ኮምፒውተር ላይ ባጋጠመ እክል ምክንያት ለማረፍ ተገዷል።
ከዓለማችን ግዙፍ የአቪዬሽን ኩባንያዎች መካከል አንዱ የሆነው የጀርመኑ ሉፍታንዛ አየር መንገድ ተሳፋሪዎችን ከአሜሪካ ሎሳንጀለስ ወደ ፍራንክፈርት ጀርመን ይዞ እየበረረ ነበር።
ይሁንና በዚህ አየር መንገድ ላይ ካሉ ተሳፋሪዎች መካከል የአንዱ መንገደኛ ላፕቶፕ ኮምፒውተር ላይ እሳት መነሳቱ ተገልጿል።
አውሮፕላኑም ችካጎ አውሮፕላን ጣቢያ ለጥንቃቄ በሚል ለማረፍ መገደዱን አየር መንገዱ አስታውቋል።
ይህ በአንድ መንገደኛ ላፕቶፕ ላይ የደረሰው እሳት አደጋ የባሰ ጉዳት ሳያስከትል በቁጥጥር ስር እንደዋለም ተገልጿል።
በዚህ አደጋ ምክንያት በተሳፋሪዎች ላይ ለደረሰው የጉዞ መዘግየት አየር መንገዱ ይቅርታ ጠይቋል።
አውሮፕላኖች በበረራ ላይ እያሉ አስቂኝ እና ቀላላ በሚመስሉ ክስተቶች ምክንያት አብራሪዎች በድንገት ወደ ምድር በመውረድ አውሮፕላን ያሳርፋሉ።
በድንገት በሚከሰት ምጥ፣ ተሳፋሪዎች እርስ በርሳቸው እና ከበረራ አስተናጋጆች ጋር በሚፈጥሩት አምባጓሮ፣ በቴክኒክ ብልሽት እና በሌሎች ምክንያቶች በረራ ያቋርጣሉ።