ፖለቲካ
በለንደን ሰማይጠቀስ ህንጻ ያለደህንነት ገመድ የወጣው ግለሰብ ምን አጋጠመው?
ግለሰቡ በተለምዶ 'ቺዝ ግሬተር' የተባለውን ህንጻ ሲወጣ መንገደኞች በቪዲዮ ቀርጸውታል
ባለፈው ሀምሌ ወር ሌላ እንግሊዛዊ በደቡብ ኮሪያ ሲኡል ከተማ የሚገኘውን ከዓለም በእርዝመቱ አምስተኛ የሆነውን ሎቶ ወርልድ ታወር ሲወጣ በፖሊስ መያዙ ይታወሳል
በእንግሊዝ ለንደን ከሚገኙት ሰማይጠቀስ ፎቆች አንዱን ያለደህንነት ገመድ በመውጣት የተጠረጠረው ግለሰብ በፖሊስ ተይዞ ታስሯል።
ግለሰቡ በተለምዶ 'ቺዝ ግሬተር' የተባለውን ህንጻ ሲወጣ መንገደኞች በቪዲዮ ቀርጸውታል።
225 ርዝመት ያለውን ህንጻ ሲወጣ የደህንነት መሳሪያዎች አልተጠቀመም ያለው ፖሊስ ጣሪያው ላይ ከደረሰ በኋላ ተይዞ መታሰሩን ገልጿል።
የለንደን ፖሊስ ቺፍ ኢንስፔክተር ቶም ፊሸር ሊደንኸል ህንጻን ያለፍቃድ እና ያለደህንነት መሳሪያ በመውጣቱ ግለሰቡ ታስሯል ብለዋል።
"ፖሊሶች ጣሪያው ጫፍ ላይ በቁጥጥር ስር አውለውታል።"
የሊደንኸል ህንጻ በለንደን በእርዝመቱ ስድስተኛ ነው።
ባለፈው ሀምሌ ወር ሌላ እንግሊዛዊ በደቡብ ኮሪያ ሲኡል ከተማ የሚገኘውን ከዓለም በእርዝመቱ አምስተኛ የሆነውን ሎቶ ወርልድ ታወር ሲወጣ በፖሊስ መያዙ ይታወሳል።
ግለሰቡ የተያዘው 123 ፎቅ ካለው የሎቶ ወርልድ ታወር ህንጻ 73ኛ ፎቅ ላይ ከደረሰ በኋላ ነበር።