የለንደን ኬሚስቶች አርቲፊሻል አልኮል መስራታቸውን ገለጹ
አዲሱ ምርት የአልኮል ጥቅሞችን በማሳያሳጣ መንገድ መሰራቱ ተገልጿል
አልካሬል የተሰኘው ይህ ምርት ተጠቃሚዎችን ፈታ ከማድረጉ ባለፈ በአልኮል መጠጥ ምክንያት ይደርስ የነበሩ ጉዳቶችን ያስቀራል ተብሏል
የለንደን ኬሚስቶች አርቲፊሻል አልኮል መስራታቸውን ገለጹ፡፡
ዎል ስትሪት ጆርናል ዋና መቀመጫውን ለንደን ያደረገው ጋባ ኩባንያን ዋቢ አድርጎ እንደዘገበው አልካሬል የተሰኘ አርቲፊሻል አልኮል ሰርተዋል፡፡
ከአልኮል መጠጦች የማገኘው ገቢ ቀንሶብኛል ያለችው ጃፓን ወጣቶቿ እንዲጠጡ ማበረታታት ጀመረች
ሰዎች አልኮል መጠጥ ሲወስዱ በአእምሮ ላይ በሚፈጥረው ጉዳት ምክንያት ሰዎች ቀጥ ብለው እንዳይጓዙ፣ የራስ ህመም እንዲያጋጥማቸው፣ ንግግራቸውን እና ድርጊታቸውን እንዳይቆጣጠሩ በማድረግ ይታወቃል፡፡
አልካሬል የተሰኘው ሴንተቲክ ወይም አርቲፊሻል አልኮል ግን ከላይ የተጠቀሱትን እና ሌሎች ጉዳቶች በማያስከትል መልኩ መሰራቱን ተመራማሪዎቹ ተናግረዋል፡፡
ምርቱን እንዲጠጡ የተደረጉ በጎ ፈቃደኞች የስካር ስሜት እንደሌላቸው ነገር ግን የመዝናናት እና መፍታታት ስሜት እንደተሰማቸው እንዲሁም አስተሳሰባቸውን መቆጣጠር እና መንቀሳቀስ ላይ ምንም አይነት ችግር እንዳልገጠማቸው ተናግረዋል ተብሏል፡፡
ስሜቱ ልክ አንድ ብርጭቆ ወይን እንደመጠጣት ነው የተባለ ሲሆን ምርቱ በተለይም አልኮል መጠጣት ለሚፈልጉ ነገር ግን ጉዳቱን በመፍራት ከመጠቀም ለተቆጠቡ ሰዎች ዋነኛ ምርጫ እንደሆነ ተገልጿል፡፡
የዓለማችን ቀዳሚ የአልኮል መጠጥ ተጠቃሚ ሀገራት እነማን ናቸው?
አልካሬል አልኮል የሚያስከትላቸውን ጉዳቶች በመቀነስ ጥቅሞቹን ግን በያዘ መልኩ በቤተ ሙከራ መሰራቱን ተመራማሪዎቹ ለዚሁ ሚዲያ ተናግረዋል፡፡
አዲሱ ምርት ከፈረንጆቹ 2026 ጀምሮ ለዓለም ገበያ እንደሚቀርብ የተገለጸ ሲሆን እስከዛው ተጨማሪ ማሻሻያዎች እንደሚደረጉበት ተገልጿል፡፡
በርካቶች አልኮል መጠጥን መጠቀም ቢፈልጉም በጤና እና በአዕምሮ ላይ በሚያደርሰው ጉዳት ምክንያት አልኮልን የማያጠቀሙ ወይም የሚጠጡትን መጠን ይቀንሳሉ፡፡
አልካሬል የተሰኘው ሴንተቲክ ምርት ግን እንደ ጉበት ህመም፣ አካልን እና ስሜትን አለመቆጣጠር ጉዳቶችን እንደማያደርስ በዘገባው ላይ ተጠቅሷል፡፡