በአሜሪካ የሚፈለገው የዊኪሊክሱ መስራች ጁሊያን አሳንጅ በለንደን በእስር ቤት ተሞሸረ
ጁሊያን አሳንጅ በእስር ላይ እያለ ከተዋወቃት ጠበቃ ጋር የጋብቻ ስነ ስርዓቱን ፈጽሟል
በሰርግ ስነ ስርዓቱ ላይ አራት እንግዶች ብቻ መታደማቸው ተነግሯል
በአሜሪካ በጥብቅ የሚፈለገው የዊኪሊክሱ መስራች ጁሊያን አሳንጅ በበርካቶች ዘንድ አነጋጋሪ የሆነ የሰርግ ስነ ስርዓት ፈጽሟል።
ጁሊያን አሳንጅ የአሜሪካ ወታደራዊ ሚስጥሮች የያዙ ሰነዶች ለውጭ ኃይሎች አሳለፎ ሰጥቷል በሚል በአሜሪካ ባለስልጠናት በኩል ጥርስ የተነከሰበትና 18 በሚሆኑ ክሶች ዋና ተፈላጊ ሰው መሆኑ ይታወቃል።
ምንም እንኳ የ50 ዓመቱ አሳንጅ በአሜሪካ የቀረበለትን ክስ ውድቅ ቢያደረግም፤ አድርጎታል ከተባለ ድርጊት ጋር በተያያዘ ለ7 ዓመታት በለንደን በሚገኘው የኢኳዶር ኤምባሲ፤ እንዲሁም እንደፈረንጆቹ ከ2019 አንስቶ አስካሁን ድረስ በደቡብ ምስራቅ ለንደን በሚገኘው የቤልማርሽ እስር ቤት እንዲታሰር ምክንያት ሆኖታል።
የኢኳዶር ኤምባሲ የሰባት ዓማታት የአሳንጅ ቆይታዎች ከባድና ጣፋጭ አንደነበሩም ነው የሚገለጸው። ለምን ቢባል አሳንጅ አሁን ላይ ያገባትን ፍቅረኛውን ያገኘበት ስፍራ ነበርና።
ነገሩ እንዲህ ነው፤ አሳንጅ እንደፈረንጆቹ በ2015 በኢኳዶር ኤምባሲ ውስጥ እያለ አንዲት በአድሜ በአስር ዓመታት ከሱ እምታንስ ሞሪስ የተባለች መልከ መልካም ጠበቃ ጋር የተዋወቀ ሲሆን፤ ትውውቁም ጊዜያዊ አልነበረም።
በእስር ቤት የተጀመረው ትውውቅ ፍቅር ተጨምሮበት ዛሬ ላይ አራት ልጆች ማፍራት የቻለ ትልቅ ቤተሰብ ሆኗል።
እናም ያ በእስር ቤት የተጀመረው ፍቅር አሁን ላይ ወደ ጋብቻ በመቀየሩ በርካቶችን እያነጋገረ ነው።
የሰርግ ስነ ስርዓቱ ሰው መግደልን ጨምሮ ከባባድወ ወንጀሎችን የፈጸሙ ታራሚዎች በሚታሰሩበት የለንድ ማረቢያ ቤት ውስጥ መካሄዱ ደግሞ ሌላኛው አነጋጋሪ ጉዳይ አድርጎታል።
የጋቻ ስነ ስርዓቱ በታራሚዎች መጠየቂያ ሰዓት ላይ አራት እንግዶች፣ ሁለት ምስክሮች እና ሁለት የጥበቃ ሰራተኞች ብቻ በታደሙበት ነው የተካሄደው።
አሳንጅ ለሰርጉ በብሪታንያዋ ፋሽን ዲዛይነር ቪቪን ዌስትዉድ የተነደፈውንና "ሴልትስ" በመባል የሚታወቀው የስኮትላንድ ካባ በመልበስ ከፍቅር አጋሩ ሞሪስ ጋር መሞሸሩም ተነግሯል።