‘ለንደን’- የዓለማችን የህገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውር ዋና ከተማ
ዓለም አቀፍ ህገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውር የሚካሄደው በቅንጦት ቤቶች ላይ ኢንቨስት በሚደረግ መዋእለ ነዋይ ነው
ለንደን የህገ-ወጥ ገንዘብ የገንዘብ ዝውውር ማእከል መሆን የጀመረችው ከማርጋሬት ታቸር ዘመን ጀምሮ ነው
የብሪታኒያዋ መዲና ለንደን የዓለማችን ከፍተኛ ህገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውር የሚካሄድባት ዋነኛዋ ከተማ መሆኗን ጥናቶች አመለከቱ፡፡
የለንደን የትራንስፓረንሲ ኢንተርናሽናል ህገ ወጥ የገንዘብ ዝውውሩ በቤቶች ዘርፍ ኢንቨስት በሚደረግ መዋእለ ነዋይ የሚፈጸም መሆኑ ን አስታውቋል።
እንደ ዌስት ሚኒስተር፣ ኬንሲንግተን እና ቼልሲ ያሉ በማዕከላዊ ለንደን የሚገኙ ሪል እስቴቶች የዚሁ ሆነኛ ማሳያ መሆነቸውም ማክስዌል በአብነት አስቀምጧል፡፡
የመሬት መዝገብ ቤት ማእከል መረጃ ላይ በመመርኮዝ የብሪቲሽ ጋዜጣ ያቀረበው መረጃ እንሚጠቁመው ከሆነ ፤ አሁን ላይ “አጠራጣሪ”የሆኑና የውጭ ግንኙነቶች ባላቸው ኩባንያዎች አማካይነት የተከናወኑ የመኖሪያ ቤቶች ግዥዎች መጠን ወደ 122 ቢሊየን ፓውንድ ደርሷል።
እንደ አኃዙ ከሆነ፣ በብሪታንያ ውስጥ ስማቸው ሳይገለጽ 6 ነጥብ 7 ቢሊዮን ፓውንድ የሚገመቱ ወደ 84 ሺ ገደማ ቤቶች ይገኛሉ፡፡
ከዚህም በተጨማሪ በሙስና በተከሰሱ ሩሲያውያን የተገዙ ወይም ከ "ክሬምሊን" ጋር የጠበቀ ግንኙነት እንዳላቸው የሚነገርላቸው 1ነጥብ 5 ቢሊዮን ፓውንድ የሚገመቱ ወደ 150 የሚጠጉ የንብረት ይዞታዎች እንዳሉም የጋዜጣው መረጃ ያመላክታል፡፡
በብሪታኒያ የሚሰተዋለውን ህገ-ወጥ የግንዘብ ዝውውር ለመግታት የብሪታኒያ የፍትህ አካላት የተለያዩ እርምጃዎች ሲወሰዱ መቆየታቸውም ነው የተገለጸው፡፡
በነዳጅ ሃብት የበለፀጉትና የናይጄሪያ “ዴልታ” ግዛት የቀድሞ ገዥ ጄምስ ኢቦሪ፤ በህገወጥ የገንዘብ ዝውውር ወንጀል ተከሰው የ13 አመት እስራት ከተፈረደባቸው ጥቂቶቹ መሆናቸውም ጋዜጣው ዘግቧል።
ሌላው የብሪታንያው ጋዜጣ ዘ ኢንዲፐንደንት ደግሞ “እነዚህ ገንዘቦች የሚተዳደሩት በብሪቲሽ የባህር ማዶ ግዛቶች እና ጥገኛ ግዛቶች ውስጥ ባሉ ኩባንያዎች ነው” ሲል ዘግቧል።
በእነዚህ የባህር ዳርቻ የፋይናንስ ማእከሎች የሚሰጠው ሚስጥራዊነት ብዙውን ጊዜ የንብረት ባለቤትነትን ለመደበቅ በሚፈልጉ ሰዎች የሚጠቀሙት ዘዴ መሆኑንም አክሏል፡፡
የፋይናንሺያል ታይምስ ዘገባ እንደሚያመለክተው ከሆነ፤ ለንደን የህገ-ወጥ ገንዘብ የገንዘብ ዝውውር ማእከል መሆን የጀመረችው በማርጋሬት ታቸር የፋይናንስ አገልግሎት ዘርፍን ነፃ ማድረግ ሲጀምሩ ነው፡፡
በዚህ የተነሳም በጊዜ ሂደት የህገ-ወጥ ዝውውሩን ለመቆጣጠር በሚል ከቀድሞ ጠቅላይ ሚኒሰትር ቶኒ ብለየር ጀምሮ እስከ ዴቪድ ካሜሩንና ሌሎች ቀጥለው የመጡ መሪዎች የተለያዩ ጥረቶች ቢደረጉም ተስፋ ከማድረግ ውጭ ይህ ነው የሚባል ለውጥ ማምጣት አልተቻለም፡፡