ሚስቱን ለ26 ዓመታት የቤት እመቤት ያደረገው ባል 96 ሺህ ዶላር ካሳ እንዲከፍል ተፈረደበት
ሚስትየዋ ልጃቸውን እና ቤታቸውን ስትንከባከብ እሱ ግን ሲማር እና ስራ ሲያማርጥ ነበር ተብሏል
ፍርድ ቤቱም በ26 ዓመታት ውስጥ ለደረሰባት ጉዳት 96 ሺህ ዶላር እንዲከፈላት ወስኖላታል
ሚስቱን ለ26 ዓመታት የቤት እመቤት ያደረገው ባል 96 ሺህ ዶላር ካሳ እንዲከፍል ተፈረደበት፡፡
በስፔኗ ፖንቴቬድራ ግዛት የሚኖሩ ባልና ሚስቶች ከሰሞኑ ወደ ፍርድ ቤት አምርተዋል፡፡
እነዚህ ባልና ሚስቶች በ1996 ተጋብተው በትዳር ይኖሩ ነበር የተባለ ሲሆን አሁን ላይ ትዳራቸው በፍቺ ተጠናቋል፡፡
ለ26 ዓመታት በቆዩበት የትዳር ህይወት አንድ ሴት ልጅ ያፈሩ ሲሆን በትዳር በቆዩባቸው ጊዜያት ሚስትየዋ ልጃቸውን እና ቤታቸውን በመንከባከብ አሳልፋለች ተብሏል፡፡
ይህ ትዳር በፍቺ መፍረሱን ተከትሎም ሚስትየዋ እኔ በትዳር ውስጥ በነበርንባቸው ጊዜያት ውስጥ የቤት ውስጥ ስራዎችን ብቻ እንድሰራ አድርጎኛል እሱ ግን ሲማር፣ ስራ ሲያማርጥ ቆይቷል አሁን ላይ እኔ ገቢ የለኝም ካሳ ያስፈልገኛል ስትል ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤት እንደወሰደችው ተገልጿል፡፡
270 ጥንዶችን ያጋቡት ስፔናዊ ለትዳር የወንዶች ቁመት ወሳኝ ነው ይላሉ
26 ዓመት ላገለገልኩበትም 130 ሺህ ዶላር ካሳ ያስፈልገኛል ያለችው ይህች ተከሳሽ በክርክራቸው መጨረሻም 96 ሺህ ዶላር ካሳ እንዲከፈላት ተወስኖላታል፡፡
ለሴት ልጃቸው የሚያስፈልገውን ወጪ በጋራ እንዲሸፍኑ፣ ባልየው ለቀድሞ ሚስቱ በየወሩ 381 ዶላር ለሶስት ዓመታት እንዲከፍል በፍርድ ቤት ተፈርዶበታል ሲል ኦዲቲ ሴንትራል ዘግቧል፡፡
በአውሮፓ በትዳር ጊዜያቸው የቤት እመቤት ሆነው ያሳለፍ የቀድሞ ሚስቶች ባሎቻቸውን በመክሰስ ላይ ሲሆኑ ከሁለት ዓመት በፊት በስፔን እና ፖርቹጋል ለቀረቡ ተመሳሳይ ክሶች እያንዳንዳቸው 204 ሺህ ዶላር 72 ሺህ ዶላር ካሳ እንዲከፈላቸው ተወስኖላቸዋል፡፡