በቻይና በወጣትነታቸው ትዳር ለሚመሰርቱ ማበረታቻ ጉርሻ ቀረበ
እርምጃው እየቀነሰ ለመጣል የወሊድ ምጣኔ መላ ለማበጀት ነው ተብሏል
ማበረታቻው የልጆች እንክብካቤ፣ የትምህርትና ሌሎችንም ድጋፎች የሚያካትት ነው
በምስራቅ ቻይና አንድ ግዛት ሙሽራዋ 25 ዓመትና ከዚያ በታች ከሆነች ለጥንዶች አንድ ሽህ ይዋን ሽልማት ማዘጋጀቱን አስታውቋል።
የአከባቢው አስተዳደር እየቀነሰ ለመጣል የወሊድ ምጣኔ መላ ለማበጀት የተወሰደው እርምጃ ነው ተብሏል።
የቻንግሻ ግዛት አስተዳደር ባለፈው ሳምንት በይፋዊ የዊቻት ገጹ ያወጣው ጉርሻ "ለመጀመሪያ ትዳሮች አግባብ ያለው የትዳር ጥምረትንና ውልደትን" ለማበረታታት ነው ብሏል።
እርምጃው ልጅ ላላቸው ጥንዶች ደግሞ የልጆች እንክብካቤ፣ የትምህርትና ሌሎችንም ድጋፎች የሚያካትት እንደሆነ ተነግሯል።
ከስድስት አስርት ዓመታት በኋላ ለወረደው የቻይና የወሊድ ምጣኔ እና ፈጣን ለሆነው እርጅና መንግስት የተለያዩ መፍትሄዎችን ለማበጀት እየተጣደፈ ነው።
በዋናነትም ማበረታቻዎች እየቀረቡ ሲሆን፤ የገንዘብ ጉርሻና የልጆች እንክብካቤ ድጋፍ ተጠቃሽ ናቸው።
የቻይና ህጋዊ የትዳር እድሜ ለወንዶች 22፤ ለሴቶች 20 ዓመት ነው። ሆኖም ትዳር የሚመሰርቱ ሰዎች ቁጥር እያሽቆለቆለ ነው መባሉን ሮይተርስ ዘግቧል።
ይህም የወሊድ ምጣኔ እንዲወርድ ያደረገ ሲሆን፤ የሀገሪቱ ፖሊሲ ያላገባች ሴት ልጅ እንድትወልድ የሚያበረታታ ነው ተብሏል።
በ2022 የትዳር ምጣኔ በክብረ ወሰን በመቀነስ 6.8 ሚሊዮን ደርሷል ነው የተባለው። በ2021 ከነበረው ጋብቻ በ800 ሽህ ዝቅ ማለቱ ተነግሯል።
ይህም 1986 ከነበረው ዝቅተኛ ምጣኔ የወረደ ነው።