ፌስቡክ የተቀጣውን ከ229 ሺህ ዶላር በላይ ገንዘብ ለሩሲያ ከፈለ
ፌስቡክ በሩሲያ ጥያቄ መጥፋት የነበረባቸው ይዘቶች ባለመጥፋታቸው ነው ገንዘቡን የተቀጣው
ፌስቡኩ ሜታና የጎግሉ አልፋቤት ኩባያዎች በሩሲያ ጉዳይ በቀጣይ ሳምንት የፍርድ ሂደት እንዳላቸው ተገልጿል
ፌስቡክ በሩሲያ ጥያቄ መጥፋት የነበረባቸው ይዘቶች ባለመጥፋታቸው የተጣለበትን የቅጣት ገንዘብ መክፈሉ ተገለጸ።
ፌስቡክ ሞስኮ ሕገወጥ ነው ብላ ያመነችውን ይዘት መሰረዝ ባለመቻሉ 17 ሚሊዮን ሩብል ወይም 229 ሺ 643 ዶላር ዕዳ መክፈሉን ሮይተርስ ኢንተርፋክስ የዜና አገልግሎትን ተቅሶ ዘግቧል።
ፌስቡክን እና ሌሎች መተግበሪያዎችን በአንድ ላይ ያቀፈው ሜታ ከአልፋቤት ጎግል ጋር በሚቀጥለው ሳምንት የፍርድ ሂደት እንዳላቸው ተገልጿል።
ለዚህ መንስዔ የተባለው ደግሞ ኩባንያው በተደጋጋሚ የሩስያን የይዘት ህግ ይጥሳል በሚል በመጠርጠሩ ነውም ተብሏል።
በዚህም መሰረት ኩባንያው በሩሲያ ከሚያገኘው ትርፉ ውስጥ በመቶኛ ሊቀጣ እንደሚችል ተገልጿል።
ሩሲያ በፌስቡክ ላይ የተጣለውን የ 17 ሚሊዮን ሩብል ገንዘብ ለመሰብሰብ የፍርድ አስፈጻሚዎችን ጥቅምት ላይ መላኳን ነው መገናኛ ብዙኃን ያስታወቁት።
ከዛሬ ጀምሮ ተጨማሪ የህግ ማስፈጸም ሂደቶች እንደማይኖሩ የፌዴራል ሕግ አስፈጻሚዎች አገልግሎት ዳታ ቤዝ አስታውቋል።
ፌስቡክ ለሩሲያ በቅጣት መልክ ከፍሏል የተባለውን ገንዘብ በተመለከተ እስካሁን ያወጣው መግለጫ አለመኖሩን ሮይተርስ ዘግቧል። የሩሲያው መተግበሪያ ቴሌግራምም ለሩሲያ 15 ሚሊዮን ሩብል እንዲከፍም ተወስኖበታል ተብሏል።
ይሁንና የቴሌግራም መተግበሪያ በዚህ ጉዳይ ላይ እንደፌስቡክ ሁሉ ያወጣው መግለጫ የሌለ ሲሆን ምላሽ እንዲሰጥ ተጠይቆም ምለሽ እንዳልሰጠ ተገልጿል።