ጎግል የተቀጣው የተከለከለ ይዘት ያላቸውን ልጥፎች (ፖስት) ለማስወገድ ባለመቻሉ ነው
ሩሲያ በግዙፉ የአሜሪካ የቴክኖሎጂ ኩባንያ ጎግል ላይ የ7 ነጥብ 2 ቢሊዮን ሩብል (98 ሚሊዮን ዶላር) ቅጣት አስተላለፈች፡፡
ሞስኮው ጎግልን የቀጣችው በህግ የተከለከለ ይዘት ያላቸውን ልጥፎች (ፖስትስ) ለማስወገድ ባለመቻሉ ነው፡፡
ጎግል ያልተፈቀዱ ናቸው የተባሉትን ተደጋጋሚ ልጥፎች ያለማንሳቱን ጉዳይ የተመለከተው የሞስኮው ከፍተኛ ፍርድ ቤት ነው ዓመታዊ ገቢውን ከግምት ውስጥ ያስገባ ነው የተባለለትን ውሳኔ የሰጠው እንደ ኢንተርፋክስ ኒውስ ዘገባ፡፡
ኢትዮጵያ ፌስቡክንና ትዊተርን በሀገራዊ የማህበራዊ ትስስር ገጽ የመተካት እቅድ እንዳላት አስታወቀች
የጎግል እናት ኩባንያ አልፋቤት ኢንክ. ቅጣቱን እንዲከፍልም አዟል፡፡
ሩሲያ በጎግል ላይ እንዲህ ዐይነት እርምጃን ስትወስድ ይህ የመጀመሪያ አይደለም፡፡ ከአሁን ቀደምም የ2 ሚሊዮን ሩብል ቅጣት ጥላበት ነበር፡፡ ሆኖም ይህኛው ከፍተኛው ነው ተብሏል፡፡
ኩባንያው በተላለፈበት ቅጣት ላይ አቤቱታ ሊያቀርብ እንደሚችልም ተነግሯል፡፡
ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ግዙፍ የኢንተርኔት ኩባንያዎች የሃገሪቱን ህግ እየተላለፉ ነው ሲሉ ደጋግመው ከመውቀስም በላይ የሩሲያ ተጠቃሚዎቻቸውን መረጃ ማዕከላትን ገንብተው በዚያው በሃገራቸው እንዲያከማቹ ደጋግመው ተናግረዋል፡፡
ነገር ግን ይህ ጫናዎችን ለማድረግ በማሰብ ነው የሚሉ ትቶችን አስተናግዷል፡፡
የሜታ ኩባንያ ንብረት የሆነው ፌስቡክም ተመሳሳይ ክስ አለበት፡፡ ክሱ ዛሬ አርብ የሚታይም ይሆናል፡፡