የአውሮፕላን ጉዞ ቲኬት ሳይገዛ ወደ ሁለት ከተሞች የበረረው ሰው
ግለሰቡ ከጀርኗ ሙኒክ ወደ ስዊድን ስቶኮልም ያለምንም ወጪ ተጉዟል
በመጨረሻም በፖሊስ የተያዘው ይህ አነጋጋሪ ሰው እንዴት ሊጓዝ እንደቻለ ምርመራ እየተደረገ ነው
የአውሮፕላን ጉዞ ቲኬት ሳይገዛ ወደ ሁለት ከተሞች የበረረው ሰው፡፡
የኖርዌይ ዜግነት ያለው ይህ ስሙ ያልተጠቀሰው ሰው ከጀርመን ዋና ከተማ ሙኒክ ወደ ሀምቡርግ እና ስቶኮልም ያለ ምንም የጉዞ ቲኬት ተጉዟል፡፡
ግለሰቡ የአውሮፕላን ቲኬት ሳይገዛ የጸጥታ ሀይሎች ሳይዙት ወደ ሁለት ከተሞች መጓዙ ግርምትን ጭሯል፡፡
ግለሰቡ የተጓዘባቸው አውሮፕላን ጣቢያዎች ሰዎች ያለ ቲኬት ጉዞ እንዳይጓዙ የሚከለክሉ ሰው አልባ ቴክኖሎጂዎች በስራ ላይ የነበሩ ሲሆን ይህ ሰው እነዚህ ሁሉ አልፎ ለመጓዝ በቅቷል፡፡
ዘግይቶ በተደረጉ ማጣራቶች ግለሰቡ ትክክለኛ የጉዞ ቲኬት ገዝተው ቸክ ኢን ሲያደርጉ ለቸክኢን ማሽኑ በቂ ጊዜ ሳይሰጥ ሰዎቹን ተከትሎ ወዲያውኑ አብሮ ወደ አውሮፕላኖቹ መቀላቀሉ ተረጋግጧል፡፡
ሙሽሪት 3 ኪሎግራም ወርቅ ጥሎሽ ያገኘችበት አነጋጋሪው የቱርክ ሰርግ
ይህ ግለሰብ ማጭበርበሩ የተደረሰበት እንደለመደው በነጻ ሊጓዝ ወደ አውሮፕላን ሲገባ የበረራ አስተናጋጆቹ ወንበሮች ሁሉ መያዛቸውን ባዩ ጊዜ ዳዩን ለጸጽታ ሀይሎች በመጠቆማቸው እንደሆነ ቢልድ ዘግቧል፡፡
የስዊድን ፖሊስ ተጠርጣሪውን በቁጥጥር ስር ያዋለ ቢሆንም ግለሰቡ ያደረሰው ጉዳት ወይም የደቀነው ስጋት የለም በሚል ከእስር ለቆታል፡፡
የጀርመን ፖሊስ ግን ግለሰቡ ወደ ሁለት ከተሞች ሲበር የጸጽታ ሀይሎች ቢያንስ ማንነቱን የሚያሳይ መታወቂያ እንዲያሳይ ለምን እንዳልጠየቁት ምርመራ በማድረግ ላይ መሆኑን አስታውቋል፡፡