“ሶፊያ” በሚል መጠሪያ የምትታወቀው ሮቦት በብዛት ልትመረት ነው
ኢትዮጵያን ጨምሮ ከተለያዩ ሀገራት የተወጣጡ የኮምፒውተር ሳይንስ ባለሙያዎች በሶፊያ ሮቦት ፈጠራ ላይ መሳተፋቸው ይታወሳል
በአውሮፓውያኑ በ2016 ለአለም የተዋወቀችው ሶፊያ የማህበራዊ ሚና ያላቸው ሮቦቶች ከሚባሉት ትመደባለች
መቀመጫውን በሆንኮግ ኮንግ ባደረገው እና ሀንሰን ሮቦቲክስ በተሰኘ የቴክኖሎጂ ኩባንያ በዋና መሪነት የተሰራችው ሶፍያ ሮቦት ከ50 የሚበልጡ የፊት ገለጻዎችን ማሳየት የምትችል መሆኗ ለየት ያደርጋታል።
ሶፍያ ይህን ለማድረግ ሰው ሰራሽ አስተውሎት (artificial intelligence) የሚባለውን ግሩም ቴክኖሎጂ ከማካተቷ በተጨማሪ ኢትዮጵያን ጨምሮ ከተለያዩ ሀገራት የተወጣጡ የኮምፒውተር ሳይንስ ባለሙያዎች አሻራቻን ያሳረፉባት የቴክኖሎጂ ግኝት መሆኗን የኢትዮጵያ ቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ኢኒስቲተዩት መረጃ ያመለክታል።
ከአመታት በፊት አይኮግ ላብስ በተባለው ድርጅት የታቀፉ ኢትዮጵያውን ባለሙያዎች የሮቦቷን አካል ከሰራው ሀንሰን ሮቦቲክስ ኩባንያ ጋር በመተባባር ለሶፍያ የሰው ሰራሽ አስተውሎት ቀመሮችን በማዘጋጀት ስራ ላይ በዋናነት ሲሰራ መቆዩታቸው የሚታወቅ ሲሆን ሮቦቷን ወደ ውጤት በማምጣት ሂደት ላይም የራሳቸውን ተሳትፎ ማድረጋቸውን ኢኒስቲትዩቱ አስታውቋል።
እንደአውሮፓውያኑ በ2016 ለአለም የተዋወቀችው ሶፊያ ሮቦት የማህበራዊ ሚና ያላቸው ሮቦቶች ከሚባሉት የምትመደብ ቢሆንም ከሷ በፊትና ከሷ በኋላ ከተሰሩት ማሽኖች እጅግ የሚለይ ባህሪዎችና ገፅታዎች የተላበሰች ናት።
እስካሁን በዚህ ዘርፍ ከተሰሩት ማሽኖች ከሰዎች ጋር ባላት ግንኙነት እና እንደየሁኔታው በሚያጋጥሟት ክስተቶች እንደ መቆጣት፣ ማዘን እና መደሰት ያሉ ሰውኛ ባህሪዎችን ለመሳየት መቻሏ ሶፊያን ከሌሎች የማህበራዊ ሚና ካላቸው ሮቦቶች ለየት የሚደርጋት ነው።
ሶፊያ በአለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ እውቅና ያላት እና በማህበራዊ ሚና ላይ ለሰዎች ይበልጥ የቀረበች ሮቦት ብትሆንም በብዛት የመመረት እድል ስላልነበራት ወደብዙዎች መድረስ አለመቻሏን የሚያስረዱት የሀንሰን ሮቦቲክስ መስራች ዴቪድ ሃንሰን፤ አሁን ላይ ከኮቪድ መምጣት ጋር ተያይዞ ሮቦቷን በብዛት አምርቶ ወደገበያ ለማቅርብ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።
የሶፍያ ሮቦት እስከአመቱ መጨረሻ በሺዎች በመማረት ለገበያ ለማቅርብ እየሰራ መሆኑን የሚናገሩት ዴቪድ ሃንሰን፤ “አሁን ባለንበት አለም እንደሶፊያ ያሉ ማህበራዊ ሚና ያላቸው አውቶሜትድ ማሽኖች አቅመ ደካሞችን ያለመሰልቸት ለመርዳት እና የታመሙ ሰዎችንም ለማገዝ ትልቅ ሚና አላቸው” ይላሉ።
ሶፊያ ተግባሮችን ለመከወን የሚስችል የስሜት ተለዋዋጭነት እና የበዛ የቋንቋ ክህሎት የታከለባት ሮቦት እንደመሆኗ መጠን ተቀባይነቷን እንደሚጨምረው የባለሙያዎች ይናገራሉ።
“ሶፊያ” ሮቦት ከሶስት ዓመታ በፊት ወደ ኢትዮጵያ መጥታ እንደነበረ የሚታወስ ሲሆን፤ በወቅቱም የተለያዩ መርሃ ግብሮች ላይ ታማ በበርካታ ኢትዮጵያውያን ተጎብኝታለች።
ሶፊያ ሳዑዲ አረቢያዊ ዜግነትን ያገኘች የመጀመሪያዋ ሮቦት መሆኗም አይዘነጋም።