የሚስቀው ሮቦት ፕሮጀክት ሮቦቶችን ከሰው ልጅ ጋር የማመሳሰል እቅድ አንዱ ካል ነው
የጃፓን ተመራማሪዎች ከዚህ በፊት ያልተመለደ “በሰዎች ቀልድ የሚስቅ ሮቦት” መስራታቸውን ከሰሞኑ አስታውቀዋል።
ሮቦቱን ሳቅ ያስተማሩት የጃፓን ክዮቶ ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪዎች ሲሆኑ፤ ዋና አላማዉም ሮቦቶች የበለጠ ከሰው ልጆች ጋር ለማመሳሰል እንደሆነም ተነግሯል።
ክዮቶ ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪዎች ሮቦቱ ትክክለኛ የሰው ልጆችን ሳቅ እንዲስቅ ለማለማመድም ሰው ሰራሽ ክህሎት (አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ) መጠቀማቸውን አስታውቀዋል።
ተመራማሪዎቹ ኤሪካ የሚል ስያሜ ባለው ሮቦት ላይ ሳቅን የማስተማር ስራውን እየሰሩ ሲሆን፤ ይህ ስራም በሰዎች እና በሮቦቶች መካከል ያለው ንግግሮች የበለጠ ተፈጥሯዊ እንዲመስሉ እንደሚያደርግ ተስፋ ሰንቀዋል።
ርዝመታቸው ከሁለት እስከ ሶሰስተ ደቂቃ የሚቆዩ ንግግሮች በሰዎች እና በኤሪካ ሮቦት መካከል የተደረገ ሲሆን፤ ይህም አዲሱን ሲሰተም ለመመኮር እንደተካሄደ እና ስራውም በጎ ውጤት እንደተገኘበት አስታውቀዋል።
ሮቦቶቹ የበለጠ ከሰዎች ጋር እንዲግባቡ እና በቀልዶች የምር እንዲስቁ ለማስቻል አሁንም ቀሪ ስራች እንደሚቀሩ አስታውቀዋል።
በሰዎች እና በሮቦቶች መካከል ልክ ንደጓደኛ መደበኛ ንግግሮች እንዲኖሩ ለማስቻል እየሰሩ መሆኑን ያስታወቁት ተመራማሪዎቹ፤ ይህንን እውን ለማድረግ እን ከ10 እስከ 20 ዓመት ሊያስፈልገን ይችላል ብላዋል።