“ኒንጃ” የሚል ቅጽል ስም የተሰጠው “M-81” ወታደራዊ ሮቦት ታንኮችን አነፍንፎ የሚያወድም ነው
ሩሲያ እያካሄደች ባለው የ2022 ዓለም አቀፍ የጦር መሳሪያ ኤክስፖ ላይ የተለያዩ ወታደራዊ ቁሰቁሶችን ይፋ አድርጋለች።
ሩሲያ ይፋ ካደረገቻቸው ወታደራዊ መገልገያዎች ውስጥ “ኒንጃ” የሚል ቅጽል ስም የተሰጠው “M-81” ወታደራዊ ሮቦት ውሻ የበርካቶችን ቀልብ መሳቡ ተነግሯል።
“M-81” ወታደራዊ ሮቦት ዓለም አቀፍ የጦር መሳሪያ ኤክስፖው ላይ ሲንቀሳቀስ፣ ሲሮጥ እንዲሁም ሲተኛ እና ሲገለባበጥ ታይቷል።
የሮቦቱ ማሽን ኢንተሌክት በተባለ ኩባያ አማካኝነት የተመረተ ሲሆን፤ የጦር መሳሪያ የመሸከም እና የመተኮስ አቅም ያለው መሆኑም በስፋት ተነግሯል።
“M-81” ወታደራዊ ሮቦት የተሰጡትን ኢለማዎች ማጥቃት እና የቅኝት ስራዎችን ጨምሮሌሎች የደህንነት ስራዎችን በቀላሉ የሚከውን መሆኑንም የኩባንያው ቃል አቀባይ ተናግረዋል።
በኤክስፖው ላይ “M-81” ወታደራዊ ሮቦት “RPG-26” የተባለ የፀረ ታንክ ሮኬት ማስወንጨፊያ መሳሪያ ታጥቆ የታየ ሲሆን፤ የሮኬት ማስወንጨፊያ መሳሪያው እስከ 3 ኪሎ ግራም የሚመዝን ነው።
ሮቦት ውሻው ሙሉ በሙሉ በጥቁር ጨርቅ የተሸፈነ ሲሆን፤ ለመመልከቻ የሚረዳው የኦፕቲካል ሴንሰር ስፍራው ብቻ ክፍት የተተወ ነው።