በስዊዝ ቦይ ውስጥ ተሰንቅራ መተላለፊያ የዘጋቸው መርከብ እንደገና ተንሳፋ መንቀሳቀስ ጀመረች
ስዊዝ ቦይን የዘጋችው መርከብ ተንቀሳቀሰች፤ መተላለፊያውም ተከፈተ
በዓለም ትላልቅ የንግድ መርከቦች የሚንቀሳቀሱበትን የግብጹን የስዊዝ ቦይ ለእንቅሰቃሴ ዝግ እንዲሆን ምክንያት የሆነችው መርከብ ተንቀሳቅሳለች፤ መተላለፊያውም ተከፍቶ መርከቦች እየሄዱበት ነው፡፡
በዛሬው እለት ጠዋት ኢንች ኬፕ ሺፒንግ አገልግሎት እንዳስታወቀው በግብጹ የስዊዝ ቦይ ላይ ተሰንቅራ መተላለፊያ የዘጋቸው ‘ኤቨር ጊቭን’ የተሰኘችው መርከብ እንደገና መንሳፈፍ ችላለች፡፡
የኢንች ኬፕ ሺፒንግ አገልግሎት በትዊተር ገጹ እንዳስታወቁት መርከቧን ለማንሳፈፍ ለተሰራው ስራ በአካባቢው ሰዓት ከጠዋቱ 4፡30 ተጠናቆ፣ በአሁኑ ወቅት ደህንነቷ እየተጠበቀ ነው ፡፡ የመርከብ መከታተያ አገልግሎት “መርከብ ፈላጊ” የመርከቧን ሁኔታ በድረ-ገጹ ላይ ቀይሮታል ፡፡
የአገልግሎት ድርጅቱ እንዳስታወቀው ዛሬ ጠዋት ተሰንቅራ የነበረችውን የፓናማ የኮንቴነር መርከብ ለማንቀሳቀስ የማንሳፈፍ ስራ ተሰርቷል፡፡
በዓለም ላይ እጅግ ከተጨናነቁ የንግድ መርከብ መተላለፊያዎች አንዱ የሆነው የግብፁ ስዊዝ ቦይ መተላለፊያ ካሳለፍነው ማክሰኞ ጀምሮ የ224 ሺ ቶን ክብደት ፣ 400 ሜትር ርዝመት እና 59 ሜትር ስፋት ባለት መርከብ መዘጋቱ ይታወሳል።
መርከቧ ከቀይ ባህር ወደ ሜዲተራኒያን ባህር በሚሻገርበት ወቅት በከፍተኛ ንፋስ በድንገት በመመታት በቦዩ መተላለፊያ ላይ በጎኑ ተዘርግቶ በመቆም ቦዩ እንዲዘጋ አድርጓል፡፡ በቦዩ መዘጋት ምክንያት ከ360 ባለይ መርከቦች እንቆሙ ተገደዋል፡፡
በዓለም ትልቅ መተላለፊያ የሚባለው የስዊዝ ቦይ በመዘጋቱ በእየቀኑ የ9 ቢሊዮን ዶላር የንግድ ልውውጥ ማስተጓጎሉ ተዘግቧል፡፡ “የኤቨር ጊቭን” መርከብ ባለቤት ጃፓናዊ ለተፈጠረው የእንቅስቃሴ መስተጓጎል ይቅርታ ጠይቀዋል፡፡