በ6 ሚሊዮን ዶላር የተሸጠው የኒዮርኩ ሙዝ ጉዳይ አሁንም ማነጋገሩን ቀጥሏል
ባሳለፍነው ሳምንት በአሜሪካዋ ኒውዮርክ ከተማ በ40 ብር የተገዛ ሙዝ በጨረታ በ750 ሚሊዮን ብር መሸጡ ይታወሳል
ሙዝ ሻጩ ሰው ስደተኛ እና ድሃ መሆኑን ተከትሎ እርዳታዎች እየጎረፉለት ይገኛል
በ6 ሚሊዮን ዶላር የተሸጠው የኒዮርኩ ሙዝ ጉዳይ አሁንም ማነጋገሩን ቀጥሏል፡፡
ከአንድ ሳምንት በፊት የዓለማችን ዋነኛ የዲፕሎማሲ ማዕከል በሆነችው ኒውዮርክ ከተማ አንድ ሙዝ በጨረታ 6 ነጥብ 2 ሚሊዮን ዶላር ወይም ከ750 ሚሊዮን በላይ ብር ተሸጧል፡፡
ይህች አንድ ሙዝ በግድግዳ ላይ ከተሰቀለች በኋላ ዓለም አቀፍ ጨረታ ላይ የቀረበች ሲሆን 6 ቻይናዊው የክሪፕቶከረንሲ ነጋዴ ጀስቲን ሰን ጨረታውን በ5 ነጥብ 2 ሚሊዮን ዶላር አሸንፏል፡፡
አሸናፊው ጨረታውን ላካሄደው ድርጅት አንድ ሚሊዮን ዶላር በድምሩ 6 ነጥብ 2 ሚሊዮን ዶላር ከከፈለ በኋላ ሙዟን በዛሬው ዕለት ተመግቧል፡፡
ኒዮርክ ፖስት ዓለምን ያነጋገረውን ይህ ሙዝ የሸጠውን ሰው ቃለ መጠይቅ ካደረገለት በኋላ ትኩረት ሁሉ ወደሻጩ ሆኗል፡፡
ሻህ አላም የተባለው ሰው የ74 ዓመት ባንግላዲሽ ዜግነት ያለው ስደተኛ ሲሆን በሰዓት 12 ዶላር እየተከፈለው ከአንድ አትክልት መሸጫ ማዕከል ውስጥ ተቀጥሮ የሚሰራ ሆኖ ተገኝቷል፡፡
ደቡብ ኮሪያዊው ተማሪ 160 ሺህ ዶላር የሚያወጣ ሙዝ መብላቱ ተገለጸ
እሱ በ40 ብር ገደማ የሸጠው ሙዝ 6 ነጥብ 2 ሚሊዮን ዶላር ተሸጠ ሲባል መገረሙን እና አብደዋል ወይ የሚል ጥያቄ እንደመጣለት ተናግሯል፡፡
እያሳለፈ ስላው ህይወት በሚዲያ ላይ ከወጣ በኋላ የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም የተካሄደለት ሲሆን እስካሁን ከ8 ሺህ ዶላር በላይ ገንዘብ ተዋጥቶለታል፡፡
ሙዙን ገዝቶ በጨረታ የሸጠው ሰው ግለሰቡን የመርዳት ሀሳብ ካለው ለቀረበለት ጥያቄ “ጥበብ ችግርን አይፈታም፣ ይህን ካደረገ ግን ጥበብ ፖለቲካ ይሆናል” ሲል ምላሽ ሰጥቷል ተብሏል፡፡
ጨረታውን ያሸነፈው ቻይናዊ ቢሊየነር ጀስቲን ሰን በበኩሉ የሙዝ ሻጩን ታሪክ ካወቀ በኋላ ልቡ እንደተነካ ገልጾ 100 ሺህ ሙዝ እንደሚገዛው ቃል ገብቶለታል፡፡