ለምን ተከራከርከኝ በሚል ተማሪውን በሽጉጥ የመታው መምህር ቁጣን ቀሰቀሰ
ተማሪው መምህሩን በክፍል ውስጥ በመከራከሩ ሽጉጥ ተተኩሶበታል
የሕክምና መምህሩ ቦርሰው በፖሊስ ሲፈተሸ ተጨማሪ ጦር መሳሪያዎችን ይዞ ተገኝቷል
ለምን ተከራከርከኝ በሚል ተማሪውን በሽጉጥ የመታው መምህር ቁጣን ቀሰቀሰ፡፡
ሪሀን ሸሪፍ በእስያዊቷ ባንግላዲሽ መዲና ዳካ ከተማ ውስጥ ባለ የህክምና ኮሌጅ በመምህርነት ተቀጥሮ በመስራት ላይ ይገኛል፡፡
ይሁንና ከሰሞኑ ክፍል ውስጥ እያስተማረ እያለ ሽጉጥ በመምዘዝ የተከራከረውን ተማሪ መቷል፡፡
በተማሪው እግር ላይ የተኮሰው ይህ መምህር የቃል ፈተና እየሰጠ እያለ አንድ ተማሪ ከትምህርቱ ጋር በተያያዘ ባነሳው ጥያቄ ምክንያት አለመግባባት ከሰታል፡፡
ይህን ጊዜም መምህር ሪሀም የታጠቀውን ሽጉጥ በማውጣት በተማሪው ላይ የተኮሰ ሲሆን ተማሪውም እግሩ ላይ በደረሰበት የመቁሰል አደጋ ወደ ሆስፒታል ተወስዶ ህክምናውን እየተከታተለ ይገኛል፡፡
ዳካ ትሪቡን የተሰኘው ጋዜጣ እንደዘገበው ከሆነ መምህሩ በፖሊስ ቁጥጥርሰ ር የዋለ ሲሆን ፖሊስ ባደረገው ፍተሸ መምህሩ ተማሪውን ተኩሶ ከመታበት በተጨማሪ ሌላ ሽጉጥ ከ81 ጥይት ጋር እንዲሁም ከ12 ቢለዋ ጋር በቁጥጥር ስር አውሎታል ተብሏል፡፡
ባንግላዲሽ በማረሚያ ቤት ውስጥ 26 እስረኞችን አንቆ የገደለውን ታሳሪ ፈታች
45 ተማሪዎችን በአንድ ክፍል ውስጥ ሲያስተምር ነበር የተባለው ይህ መምህር ለምን ሽጉጥ እና ስለታማ ነገሮችን ይዞ እንደሚንቀሳቀስ እስካሁን ይፋ አልተደረገም፡፡
የ23 ዓመት ተማሪ እንደሆነ የተገለጸይ እና በመምህሩ በሽጉጥ የተመታው ተማሪም እግሩን በመታከም ላይ እንደሆነ ተገልጿል፡፡
በክፍል ውስጥ የነበሩት ቀሪ ተማሪዎች የክፍል አጋራቸው በጥይት ሲመታ በአይናቸው እንዳዩ፣ ወደ ፖሊስ እንደደወሉ እና ተጎጂው የህክምና አገልግሎት እንዲያገኝ አድርገዋል ተብሏል፡፡
የመምህሩን ድርጊት ተከትሎ በባንግላዲሽ ዋነኛ መነጋገሪያ አጀንዳ የሆነ ሲሆን በመምህሩ ላይ አስተማሪ የፍትህ እርምጃ እንዲወሰድ የሚጠይቁ ሰላማዊ ሰልፎችም እየተካሄዱ እንደሆነ ተገልጿል፡፡