ራስን የማጥፋት ወንጀል የተበራከተባቸው የዓለማችን ሀገራት እነማን ናቸው?
በደቡብ ኮሪያ ከ100 ሺህ ሰዎች ውስጥ 26ቱ ራሳቸውን እንደሚያጠፉ ተገልጿል
በጦርነት ውስጥ ያለችው ዩክሬን እና ጎረቤቷ ሉትኒያ ራሳቸውን የሚያጠፉ ዜጎች ቁጥር ከጨመረባቸው ሀገራት መካከል ተጠቅሰዋል
ራስን የማጥፋት ወንጀል የተበራከተባቸው የዓለማችን ሀገራት እነማን ናቸው?
እንደ ዓለም ጤና ድርጅት መረጃ ከሆነ እስያዊቷ ደቡብ ኮሪያ በዓለማችን ራስን የማጥፋት ወንጀል ከሚፈጸምባቸው ሀገራት መካከል ቀዳሚዋ ስትሆን በዚች ሀገር ከ100 ሺህ ሰዎች ውስጥ 26ቱ ራሳቸውን ይገድላሉ ተብሏል፡፡
ከሩሲያ ጋር ጦርነት ውስጥ ያለችው ዩክሬን፣ ቤልጂየም፣ ስሎቬኒያ፣ ክሮሽያ፣ሀንጋሪ፣ ሉትኒያ እና ጃፓን ከ100 ሺህ ሰዎች ውስጥ እስከ 16 ሰዎች ያህል ራሳቸውን ያጠፋሉ፡፡
በአሜሪካም በተመሳሳይ ራስን የማጥፋት ወንጀል እየጨመረ እንደመጣ የተገለጸ ሲሆን ከተመሳሳይ ህዝብ ቁጥር ውስጥ 14 ሰዎች ራሳቸውን እንደሚገድሉ ተገልጿል፡፡