የአድዋ ድል ለማክበር ጋዜጠኞችና አርቲስቶች ከአዲስ አባባ አድዋ ድልድይ ጉዞ ጀምረዋል
የአድዋ ድል ለማክበር ጋዜጠኞችና አርቲስቶች ከአዲስ አባባ አድዋ ድልድይ ጉዞ ጀምረዋል
ለ124 ኛው የአድዋ ድል በዓል ከተለያዩ ሙያዎች የተውጣጡ ከ300 በላይ የሆኑ ተሳታፊዎች ዛሬ ጉዞ ወደ አድዋ ጀምረዋል፡፡
ለ124 ኛው የአድዋ ድል በዓል የታሪክ ተመራማሪዎች ፣ የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች ፣ ታዋቂ ግለሰቦች እና ጋዜጠኖችን ጨምሮ ከ300 በላይ የሆኑ ተሳታፊዎች ዛሬ ከአድዋ ድልድይ መነሻ አድርገው ወደ አደዋ ጉዞ የጀመሩ ሲሆን በየቦታው ከድሉ ጋር ቁርኝት ያላቸው ቦታዎችን እንደሚጎበኙ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ያዘጋጀው የጉዞ መርሃ ግብር ያሳያል።
ከደበብ ኢትዮጵያ ወደ አድዋ ለመዝመት ጉዞ የጀመሩት አድዋ ድልድይ ላይ በመሆኑ፤ እሱን ለመዘከር ዛሬ ረፋድ ላይ ከእዚሁ ስፍራ 124ኛውን የአድዋ ድል በዓል ለማክበር ጉዞ ለሚያደርጉት ቡድን ሽኝት ተደርጓል።
በቀጣይ የጉዞ መዳረሻም በሚኒሊክ የትውልድ ስፍራ አንጎለላ ፣ አዋጅ በተነገረበት ወረ ኢሉ ፣ ውጫሌ ፣ ማይጨው እና በእንዳየሱስ ቡድኑ የሚጎበኛቸው ታሪካዊ ቦታዎች ናቸው፡፡
በመጨረሻም ከአዲስ አበባ በ1 ሺህ 10 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው አድዋ ከተማ የካቲት 23 ቀን 2012 ዓ.ም ፣ የበዓሉ የመዝጊያ ስነ ሰርዓት ይካሄዳል ተብሏል፡፡
የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትሯ ሂሩት ካሳው ለተጓዦች አሸኛኘት አድርገዋል።