ዩኤኢ በካቡል ዩኒቨርሲቲ ላይ ያነጣጠረውን ይህን ጥቃት አውግዛለች
በአፍጋኒስታን መዲና በተፈጸመ የሽብር ጥቃት 22 ሰዎች ተገደሉ
በአፍጋኒስታን መዲና ካቡል ትናንትና በተፈጸመ የሽብር ጥቃት 22 ሰዎች መገደላቸውንና በርካቶች መቁሰላቸው ተዘግቧል፡፡
የአፍጋኒስታን የሀገር ውስጥ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ እንዳሉት የጥቃቱ ፈጻሚዎች ሦስት የታጠቁ ግለሰቦች ከተገደሉ በኋላ የሽብር ጥቃቱ መቆሙን አስታውቀዋል፡፡
ጥቃቱ የተጀመረው የመንግስት ባለስልጣናት በካቡል በተዘጋጀው የኢራን የመፅሀፍት አውደ ርዕይ ስፍራ ከመድረሳቸው ጥቂት ቀደም ብሎ ሲሆን ለብዙ ሰዓታትም መቀጠሉን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡ ዓለም አቀፉ የሽብር ቡድን አይኤስ ኃላፊነቱን በወሰደበት በዚህ የሽብር ጥቃት ከሟቾቹ በተጨማሪ 22 ሰዎች መቁሰላቸውም ተገልጿል፡፡
የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች በአፍጋኒስታን ዋና ከተማ በካቡል ዩኒቨርሲቲ ላይ ያነጣጠረውን ይህን የሽብር ጥቃት አውግዛለች፡፡
በንጹሃን ዜጎች ሞት እና በንብረት ላይ የደሰውን የሽብር ጥቃት ያወገዘው የዩኤኢ የውጭ ጉዳይ እና ዓለም አቀፍ ትብብር ሚኒስቴር ፣ አቡዳቢ የሽብር ጥቃቶችን አጥብቃ ታወግለች ብሏል፡፡
በተያያዘ ዜና ትናንት ምሽት በኦስትሪያ ዋና ከተማ ቬናም በስድስት የተለያዩ ስፍራዎች ላይ በተፈጸመ የሽብር ጥቃት ሦስት ሰዎች መገደላቸውንና 15 ሰዎች መቁሰላቸውን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡ ጥቃቱ የተፈጸመው በእስላማዊው ጽንፈኛ ቡድን አይኤስ ደጋፊ እና በግብረአበሮቹ እንደሆነም የሀገሪቱ ባለሥልጣናት ገልጸዋል፡፡ በጥቃቱ ምን ያህል ሰዎች እንደተሳተፉ በግልጽ ባይታወቅም ጥቃቱን ከፈጸሙት ግለሰቦች አንዱ በፖሊስ የተገደለ ሲሆን ሌሎቹን ፖሊስ እያፈላለጋቸው ነው፡፡