ኢሰመኮ የግድያውና የሰራዊቱ መውጣት ምክንያት እንዲታወቅ መንግስት ነጻ ምርመራ እንዲጀምር ጠየቀ
የኢስመኮ ዋና ኮሚሽነር ዳኒኤል ግድያው እጅግ ዘግናኝና የሰብአዊነት መርህን የጣሰ መሆኑን ተናግረዋል
ኢሰመኮ ቁጥራቸው 60 የሚሆኑ አጥቂዎች በሶስት ቀበሌዎች የሚኖሩ አማራዎችን አጥቅተዋል ብሏል
ኢሰመኮ ቁጥራቸው 60 የሚሆኑ አጥቂዎች በሶስት ቀበሌዎች የሚኖሩ አማራዎችን አጥቅተዋል ብሏል
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በትናንትናው ምሽት ባወጣው መግለጫ በቦታው የነበረው የፌደራል ወታደሮች መውጣታቸውን ተከትሎ በኦሮሚያ ክልል በምእራብ ወለጋ በጋዋ ካንካ፣ በጊላጎጎላና በሴካ ጅርቢ ቀበሌዎች 60 አባላት ባሉት ቡድን ግድያ መፈጸሙን ከአካባቢው ምንጮች ማግኘቱን አስታውቋል፡፡
ኢሰመኮ የፌደራልና የክልል መንግስታት በግድያው ላይ በአፋጣኝ ምርመራ እንዲጀምሩና፣ ለጥቃት ተጋላጭ መሆኑ ለረጅም ጊዜ ከሚታወቀው ቦታ ሰራዊቱ እንዲወጣ የተደረገበት የጀርባ ምክንያት እንዲታወቅና የሰላማዊ ዜጎችን ደህንነት ለማስጠበቅ ተመጣጣኝ እርምጃ እንዲወስድ አሳስቧል፡፡
መግለጫው“ አጥቂዎቹ በሶስቱ ቀበሌዎች የሚኖሩ አማራዎችን አላማ አድርገዋል፡፡ ኢስመኮ ባገኘው መረጃ የተገደሉት ሰዎች ከቤታቸው ተወስደው ትምህርት ቤት ውስጥ ነው፡፡ “
መንግስት በጥቃቱ የሞቱ ሰዎች ቁጥር 32 ነው ቢልም ኢሰመኮ ግን አገኘሁት ባለው የመጀመሪያ ምርመራ ከዚህ በላይ ሊሆን ይችላል ብሏል፡፡
የኢስመኮ ዋና ኮሚሽነር ዳኒኤል በቀለ እንዳሉት የንጹሃኑ ግድያ እጅግ ዘግናኝና የሰብአዊነት መርህን የጣሰ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
“የቱንም ያህል ሀዘን ጭካኔውን ምክንያታዊ ሊያደርግ አይችልም፤ጥቃት አድራሾች ተጠያቂ ሊሆኑ ይገባል” ብለዋል ኮሚሽነሩ፡፡
ህጻናትና ሴቶችን ጨምሮ ሰለባ በሆኑበት ጥቃት የፌደራል የክልል መንግስታት በቦታው ይንቀሳቀሳል የሚባለውን ኦነግ ሽኔ ተጠያቂ አድርገዋል፡፡
እሁድ እለት የተፈጸውን ግድያ የኦሮሚያ ክልል የሽብር ድርጊት ነው ባለው ጥቃት ንጹሀን ሰለባ መሆናቸውን ቀደም ብሎ መግለጹ ይታወሳል፡፡ የአማራ ክልል በበኩሉ ንጹሃን አማራዎች መገደላቸውን ገልጾ ግድያውን አውግዟል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ማንነትን መሰረት ባደረገው ጥቃት እንዳዘኑ ገልጸው፤ ጥቃት አድራሾች ላይ እርምጃ ለመውሰድ የመከላከያ ኃይል ወደ ቦታው መሰማራቱን አስታውቀዋል፡፡