የኮፕ26 የአየር ንብረት ስብሰባ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ተራዘመ
ስብሰባውን በፈረንጆቹ 2020 ህዳር ወር በስኮቲሽ ዋና ከተማ ግላስጎው ለማካሄድ ታስቦ ነበር
በግላስጎው ሊካሄድ የነበረው የኮፕ26 የአየር ንብረት ስብሰባ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ተራዘመ
በግላስጎው ሊካሄድ የነበረው የኮፕ26 የአየር ንብረት ስብሰባ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ተራዘመ
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተ.መ.ድ) በፈረንጆቹ 2020 ህዳር ወር በስኮቲሽ ዋና ከተማ ግላስጎው ሊካሄድ የነበረው ኮፕ 26 የአየር ንብረት ስብሰባ በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት መራዘሙን የእንግለዝ መንግስት በትንናንትናው እለት አስታውቋል፡፡
“ኮሮና ቫይረስ በመላውአለም ተጽእኖ እያደረሰ ባለበት ወቅት፣ትልቅ አላማ ያለውን የኮፕ26 ማካሄድ የሚቻል አይሆን ”ብሏል መንግስት፡፡
መንግስት ባወጣው መግለጫ ስብሰባው በፈረንጆቹ 2021 ይካሄዳል ያለ ሲሆን ቀኑን ቆይቶ እንደሚያሳውቅ ገልጿል፡፡
እየጨመረ ያለውን የአለም ሙቀት ለማቆም አልሞ የነበረውና ለ10 ቀናት ይቆያል የተባለው ስብሰባው 200 የአለም መሪዎችን ጨምሮ 30000 በላይ ሰዎች ይሳተፉበታል ተብሎም ነበር፡፡
ተ.መ.ድ. በፈረንጆቹ 2018 የአለምን የአየር ንብረት አደጋ ለመቀነስ በማህበረሰብና በአለም ኢኮኖሚ ላይ መሰረታዊ ለውጥ ማድረግ እንደሚገባ አሳስቦ ነበር፡፡
በፈረንጆቹ 2030 የአለምን የካርበን ልቀት ወደ 45 ፐርስንት ዝቅ የማድረግ እንዲሁም በ2050 ደግሞ የሙቀት መጨመርን 1.5 ዲግሪ ሴልሽየስ ለማድረግ በፓሪስ ስምምነት ተቀምጧል፡፡
የተ.መ.ድ. ዋና ጸኃፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ የሰው ልጆች ህይወት መታደግ ቅድሚያ የሚሰጠው በመሆኑ የስብሰባውን መራዘም ደግፈዋል፡፡
ዋና ጸኃፊው ይህ አስገራሚ ቀውስ ሀገራት፣ማህበረሰቦችና ኢኮኖሚያዊ እድገት ለህልውና አደጋ ተጋላጭ መሆናቸውን የሚያሳይ ምሳሌ ነው ብለዋል፡፡
ሀገራት የሰው ልጆችን ጤንነት ለመጠበቅ መስራት እንዳለባቸው ዋና ጸኃፊው አንቶኒዮ ጉተሬዝ ገልጸዋል፡፡