ወጣቷ የፊንላንድ ጠቅላይ ሚኒስትር “አልኮል ጠጥታ ከጓደኞቿ ጋር ስትደንስ የሚያሳይ ቪዲዮ” አነጋገሪ ሆኗል
በሞቀ ጭፈራ ላይ እንደነበረች የገለጸችው ጠቅላይ ሚኒስትር ማሪና የ”አልኮል መጠጥ” መውሰዷ አምናለች
ማሪን፤ በ2021 የኮቪድ ገደቦችን በመጣስ በምሽት ክለብ የታየችበት አጋጠሚ አነጋገሪ ነበር
ሾልኮ የወጣውና ወጣቷ የፊንላንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ሳና ማሪን “አልኮል ጠጥታ ከጓደኞቿ ጋር ስትደንስ የሚያሳይ ቪዲዮ” አነጋገሪ ሆኗል፡፡
በዚህም የሳና ማሪን የአደናነስ ሁኔታ ጥያቄ የፈጠረባቸው የሀገሪቱ ተቃዋሚዎች፤ አደንዛዥ ዕጽ ወስዳ ከነበረ ምርመራ ማድረግ አለባት ብለዋል፡፡
ተቃዋሚዎቹ ጠቅላይ ሚኒስትሯ ያደረገቸው ድርጊት ተገቢ እንዳልሆነ ቢናገሩና እንድትመረመር ቢጠይቁም፤ የ36 አመቷ ጠቅላይ ሚኒስትር ማሪና ግን “አደንዛዥ ዕጽ አልወሰድኩም” ስትል ተደምጣለች፡፡
በሞቀ ጭፈራ ላይ እንደነበረች የገለጸችው ጠቅላይ ሚኒስትር ማሪና የ”አልኮል መጠጥ” መውሰዷን ግን አልሸሸገችም፡፡
ማሪና ከጓደኞቿ ጋር በሞቅታ ስትደንስ የሚያሳው ቪዲዮ ሾልኮ በመውጣቱ መበሳጨቷ ብትገለጽም፤ የሚቀርቡ ትችቶች ሚዛናዊ አይደሉም ብላለች፡፡
"ደንሻለሁ፣ ዘፍኛለሁ እንዲሁም ተዝናኝቻለሁ - ይህ ፍጹም ህጋዊ ነገር ነው " ስትልም ነው የቀረቡላት ትችቶች ውድቅ ያደረገችው፡፡
ሳና ማሪን ለጋዜጠኖች በሰጠችው አስተያየት " የቤተሰብ ህይወት አለኝ ፤ የስራ ህይወት አለኝ፤ ከጓደኞቼ ጋር የምዝናናበት ጊዜም አለኝ፡፡ እንደ ማንም ሰው ለመዝናነት በትክክለኛው የእድሜ ክልል የምገኝ ሰው ነኝ" የሚል ራሷን የመትከላከልበት መከራከሪያም አቅርባለች፡፡
የግል ባህሪዋ እንድትቀይር የመፈለጉ ጉዳይ ትልቅ ቁም ነገር እንዳልሆነ የምትሞግተው ጠቅላይ ሚኒስትሯ፤" የምለውጠው ነገር የለም ይህንኑ ባህሪይ እቀጥልበታለሁ፤ይህ (ባህሪይ) ተቀባይነት እንደሚያገኝ ተስፋ አደርጋለሁ" ስትልም አክላለች።
ከሁለት አመታት በፊት የ34 አመት ሳለች የፊንላንድ ከፍተኛው የመሪነት በትረስልጣን የጨበጠችው ሳና ማሪን በጣም ዘናጭና ለጥባብ ባላት ፍቅር ብዙውን ጊዜ ጭፈራ ባለባቸው ስፍራዎችና ፌስቲቫሎች የመታየት ልምድ እንዳላት ይነገርላታል፡፡
ባሳለፍነው አመት የኮቪድ ሰላባ ከሆኑ ሰዎች ጋር ተገናኝታ ስታበቃ፤ ወደ ምሽት ክለብ በመሄዷ ይቅርታ ለመጠየቅ የተገደደችበት አጋጠሚም ይታወሳል፡፡