የኔቶ አባላት ፊንላንድና ስዊድን ኔቶን እንዲቀላቀሉ የሚያስችለውን ፕሮቶኮል ፈረሙ
የኔቶ ዋና ጸኃፊ ጀንስ ስቶልተን በርግ "ክስተቱ ታሪካዊ ነው" ብለዋል
ፕሮቶኮሉ ፊንላንድ እና ስዊድን በኔቶ ስብሰባ እንዲካፈሉ እና የደህንነት መረጃ እንዲያገኙ ያስችላቸዋል
ሁለቱ ሀገራት አሜሪካን ጨምሮ የአውሮፖ ሀገራት የተሰባሰቡበትን የሰሜን አትላንቲክ የጦር ቃል ኪዳን ድርጅት(ኔቶ)ን ለመቀላቀል የሚያስችላቸው ኘሮቶኮል ተፈርሟል።
ፊንላንድና ስዊድን የኑክለር ኃይል የታጠቀውን ወታደራዊ ህብረት ለመቀላቀል የሚያስችላቸው ፕሮቶኮሎ የኔቶ አጋር በሆኑት 30 ሀገራት ተፈርሟል።
የህብረቱ ፖርላማ ውሳኔውን የሚያጸድቀው ከሆነ ኔቶ ከፈረንጆቹ 1990ዎቹ አጋማሽ ወዲህ ያደረገው ወሳኝ መስፋፋት ነው ሲል ሮይተርስ ዘግቧል።
የኔቶ ዋና ጸኃፊ ጀንስ ስቶልተን በርግ ከሁሉቱ ሀገራት ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ጋር ሆነው በሰጡት መግለጫ "ክስተቱ ታሪካዊ ነው" ብለዋል።
ዋና ጸኃፊው 32 ሀገራት ሲሰባሰቡ ህብረቱ የበለጠ ጠንካራ ይሆናል ብለዋል።
ፕሮቶኮሉ ፊንላንድ እና ስዊድን በኔቶ ስብሰባ እንዲካፈሉ እና የደህንነት መረጃ እንዲያገኙ ያስችላቸዋል።
ነገረግን በአንድ አጋር ላይ የተቃጣ ጥቃት በሁሉም ላይ እንደተቃጣ ይቆጠራል በሚለው የኔቶ ሀግ አይጠበቁም፤ይህ አንድ አመት ሊፈጅ ይችላል ተብሏል።
የኔቶ አባላት ፊርማቸውን ያኖሩት ቱርክ ሁለቱ ሀገራት ህብረቱን እንዳይቀላቀሉ ስታቀርበው የነበረውን ተቃውሞ ማንሳቷን ተከትሎ ነው። ቱርክ ተቃውሞዋን ያነሳቸው አንዳቸው ለሌላኛቸው ደህንነት ለመጠበቅ ከተስማሙ በኋላ ነው።