ስራዬን አላደነቀም በሚል ባሏን መርዛ ለመግደል የሞከረችው ሚስት
ሚስትየው የባሏን 50ኛ ዓመት ልደት ሞቅ አድርጌ ብደግስም ጥረቴን መና አስቀርቷል በሚል ነበር ለመግደል የወሰነችው
በሚወደው መጠጥ ውስጥ መርዝ የጨመረችው ሚስትም በመጨረሻ እቅዷ ሳይሰምር ለእስር ተዳርጋለች
ስራዬን አላደነቀም በሚል ባሏን መርዛ ለመግደል የሞከረችው ሚስት
በአሜሪካዋ ሚዙሪ ግዛት የሚኖሩ አንድ ባለትዳሮች ባልየው የ50 ሴቷ ደግሞ የ47 ዓመት ባለጸጋዎች ናቸው፡፡
ሚስትየው የባሏን 50ኛ ዓመት ድምቅ ባለመንገድ ለማክበር ዝግጅት ትጀምራለች፡፡
እንዳሰበችውም ይህች ሚስት የባሏን ልደት በደማቁ እንዲከበርላት ያደረገች ቢሆንም ባልየው ግን ለሚስቱ ድካም ትኩረት አልሰጠም ጥረቴንም አላደነቀም የሚል ቁጭት ይገባታል፡፡
ለዚህም መቀጣት አለበት ያለችው ይህች ሚስት በሚወደው መጠጥ ውስጥ ገዳይ ኬሚካል በመጨመር መርዛ ለመግደል ትወስናለች፡፡
የተደገሰለትን ያላወቀው ባልም ይህን መጠጥ በትንሹ ይቀምሳል፡፡ ይሁንና ባልየው የተወሰኑ የሆድ ህመሞች እንጂ ህይወቱ ሊያልፍ አልቻለም፡፡
በመጠጡ ላይ ያልተለመደ ጣዕም ያገኘው ባል ሲሲቲቪ ካሜራውን ሲያይ ሚስቱ ያልሆነ ነገር መጠጡ ውስጥ ስትጨምር ይመለከታል፡፡
ሁኔታውን በተከታታይ ሲከታተል ሚስቱ ልትተገለው እየጣረች እንደሆነ የተረዳው ባል ተንቀሳቃሽ ምስሉን ይዞ ወደ ፖሊስ ጣቢያ ያመራል፡፡
ፖሊስም በደረሰው ጥቆማ መሰረት ተጠርጣሪዋን ይዞ ሲመረምር ሚስትየው የባሏን መጠጥ ለየት ያለ ጣዕም እንዲሰጠው በማሰብ ያደረገችው እንጂ ልትገለው እየሞከረች እንዳልሆነ ትናገራለች፡፡
የጤና መድህን ክፍያ ለማግኘት ሲል ሁለት እግሮቹን የቆረጠው አነጋጋሪ ሰው
ባልየው ሚስቱ ይህን ለምን ልታደርግ ትችላለች በሚል ከፖሊስ ለቀረበለት ጥያቄ ምን አልባት ሌላ ሰው አፍቅራ ገለል እንድልላት አልያም ብሞት ሊከፈለኝ የሚችለውን የ500 ሺህ ዶላር ገንዘብ ፈልጋ ሊሆን ይችላል ሲል ግምቱን ለፖሊስ ይናገራል፡፡
ይሁንና ፖሊስ ነሚስትየው ላይ ባደረገው ተደጋጋሚ ምርመራ ለልደቱ ደክሞ ያዘጋጀሁትን ጥረት አላደነቀኝም ትኩረትም አልሰጠም ይህ አናዶኝ በጸረ አረም ኬሚካል መርዤ ልገድለው ወሰንኩ ስትል ለፖሊስ ተናግራለች፡፡