
ሚስትየው ባልየው አንድ ቀን ይመጣል በሚል ሲቀርቡላት የነበሩ የፍቅር ጥያቄዎችን ሳትቀበል ቀርታለች
ለ80 ዓመታት በሚስቱ የተፈለገው ባል
ቻይናዊቷ ዱ ሁዜን በጉዋንዡ ግዛት ነዋሪ ስትን ከሰሞኑ በ103 ዓመቷ ህይወቷ ህይወቷ ማለፉ ተገልጿል፡፡ ይህች ሴት በዚህ መንደር ያለ መሰልቸት ከ80 ዓመት በፊት ጋብቻ የመሰረተችውን ሰው ከዛሬ ነገ ይመጣል በሚል በመጠበቅ ትታወቃለች፡፡
ነገሩ እንዲህ ነው፡፡ ሁዋንግ ጀንሱ ከተባለው እና በሶስት ዓመታት ከሚበልጣት ፍቅረኛዋ ጋር በ1940 ነበር ጋብቻ የመሰረቱት፡፡
ባሏ ጀንሱ በተጋቡ ጥቂት ጊዜ ውስጥ በወቅቱ ሀገሩን ከውጭ ወረራ ለመታደግ በሚል የትጥቅ ትግል ለማድረግ ኩዋሚታንግ የተሰኘውን ቡድን ተቀላቅሏል፡፡
የአንድ ወንድ ልጅ አባት መሆኑን በትግል ላይ እያለ ያወቀው ባልየው በታሪክ አንድ ጊዜ ተመልሶ ልጁን እና ሚስቱን ጎብኝቶ መመለሱም ተገልጿል፡፡
ይሁንና ከዚያ በኋላ ከዛሬ ነገ ወደቤቱ ይመለሳል በሚል በሚስቱ ሲጠበቅ የነበረው ሰው ደብዛው የጠፋ ሲሆን ሚስቱ ግን ሳትታክት ስትጠብቀው እንደነበር ሳውዝ ቻይና ሞርኒንግ ፖስት ዘግቧል፡፡
እንደዘገባው ከሆነ ሚስትየው የባሏን መጥፋት ያወቁ አፍቃሪዎቿ የፍቅር ጥያቄ ቢያቀርቡላትም ባሌ ይመጣል እያለች ስትጠብቀው ነበር ተብሏል፡፡
ይሁንና ባልየው በሚስቱ እና በሀገሪቱ መንግስት ቢፈለግም ያለበት እንዳልታወቀ ተገልጿል፡፡ ልጃቸው ሁዋንግ ፉ አድጎ ተምሮ ሀገሩን በመመህርነት ሲያገለግል ቆይቶ ከሁለት ዓመት በፊት ህይወቱ አልፏል፡፡
ከልጅ ልጆቿ ጋር ትኖር ነበር የተባለችው ሚስትየው ሰዎች ባሏን በማሌዥያ ከዚያም በሲንጋፖር ታይቷል የሚል ወሬ መስማቷን እና አንቸድ ቀን ወደእኔ ይመጣል እንዳለች ከሶስት ቀናት በፊት ህይወቷ ማለፉ በዘገባው ላይ ተጠቅሷል፡፡
የልጅ ልጆቹም የአያታቸውን መጨረሻ ማፈላለጋቸውን እንደሚቀጥሉ የተናገሩ ሲሆን በተጓዘባቸው ቦታዎች ልጆች ካሉትም እንፈልጋለን ብለዋል፡፡