የወንድሟን ገዳይ ለማጥመድ 27 ዓመት የፈጀባት እንስት
ግለሰቧ የገዳዩን ማንነት ካወቀች በኋላም በቀሏን ለመወጣት አመቺ ጊዜ ስትጠብቅ ለሶስት ዓመታት ህመሟን ችላ ስታወራው ቆይታለች ተብሏል
አባቷ ቤተሰቡን መጠበቅ አልቻልኩም በሚል ራሱን እንዳጠፋም ተገልጿል
የወንድሟን ገዳይ ለማጥመድ 27 ዓመት የፈጀባት እንስት
ሊ ሀዩ ቻይናዊ እና በሁናን ግዛት ነዋሪ ስትሆን በፈረንጆቹ 1992 ላይ አባቷ በገንዘብ ምክንት ከአንድ ሰው ጋር አለመግባባት ይፈጠራል፡፡
በዚህም ምክንት ከአባቷ ጋር መግባባት ልቻለው ሰው የዘጠኝ ዓመት ታናሽ ወንድሟን አግቶ እንደወሰደው ተገልጿል፡፡
ወዲያው ህይወቱ አልፎ የተገኘው ይህ ወንድሟ አጋቹ እና ገዳዩ ደብዛውን ማጥፋቱን ተከትሎ በወቅቱ ግለሰቡን ህግ ፊት በማቅረብ ቅጣቱን አንዲያገኝ አልተቻለም ነበር፡፡
ልጁ የተገደለበት አባቷም ለዓመታት ቢፈልግም ገዳዩን ማግኘቱን ባለመቻሉ ምክንያት ራሱን አጥፍቷል ተብሏል፡፡
የወንድሟን መገደል አምና መቀበል የቸገራት ይህች ሴትም አባቷ ሲሞት ለቤተሰቧ ስቃይ መብዛት ምክንት የሆነውን ሰው ፍለጋ ትወጣለች፡፡
ይህ ሰውም አባቷ አስቀድሞ በነገራት ምልክቶች አማካኝነት ለዓመታት ያደረገችው ብርቱ ፍለጋ በመጨረሻም ሰምሮ ማንነቱን ትደርስበታለች፡፡
በከባድ ግድያ ወንጀል ሲፈለግ የነበረው ሰው ፖሊስ ሆኖ ተገኘ
የ47 ዓመት እድሜ ያላት ይህች ሴትም እድሜ ልኳን ልትበቀል የፈለገችውን ሰው ስትፈልግ የኖረች ሲሆን ተፈላጊ ሰው ስሙን እና የሚኖርበትን ቦታ ቀይሮ በሰላም እየኖረ እንደሆነ ትረዳለች፡፡
ስራ ፈላጊ መስላ ከምትፈልገው ሰው ጋር የተቀራረበችው ይህች ሴት በትክክል ማንነቱን ለማወቅ ለሶስት ኣመታት ስትከታተለው ቆይታለች፡፡
በእሱ ዘንድ እምነት እንዳገኘች እርግጠኛ ስትሆንም ጉዳዩን ለፖሊስ ያሳወቀች ሲሆን ተጠርጣሪውም በፖሊስ ቁጥጥር ስር ሊውል እንደቻለ የቻይና ብዙሀን መገናኛዎች ዘግበዋል፡፡
ግለሰቡ ወንድሟን እንደገደለ ለፍርድ ቤት ያመነ ሲሆን የሞት ቅጣት ይጠብቀዋል ተብሏል፡፡