እስራኤል በጋዛ የጦር ወንጀል ፈጽማለች ሲል ሂውማን ራይትስዎች ከሰሰ
እስራኤል በምላሹ ተቋሙ "ፍጹም ውሸት እና ከእውነት የራቀ" መረጃ ተጠቅሟል የሚል ክስ አቅርባበታለች
እስራኤል ጋዛ ውስጥ በፍልስጤማውያን ላይ ያደረገችው የግዳጅ ማፈናቀል ከጦር ወንጀል እና በሰብአዊነት ላይ ከሚፈጸም ወንጀል ጋር የሚስተካከል መሆኑን ድርጅቱ ባወጣው ሪፖርት አስታውቋል
እስራኤል በጋዛ የጦር ወንጀል ፈጽማለች ሲል ሂውማን ራይትስዎች ከሰሰ።
እስራኤል ጋዛ ውስጥ በፍልስጤማውያን ላይ ያደረገችው የግዳጅ ማፈናቀል ከጦር ወንጀል እና በሰብአዊነት ላይ ከሚፈጸም ወንጀል ጋር የሚስተካከል መሆኑን አለምአቀፉ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅት ሂውማን ራይትስዎች በትናንትናው እለት ባወጣው ሪፖርት አስታውቋል።
- እስራኤል በጋዛ “የዘር ጭፍጨፋ” እየፈጸመች ነው - የሳኡዲ ልኡል አልጋወራሽ
- እስራኤል በምላሹ ተቋሙ "ፍጹም ውሸት እና ከእውነት የራቀ" መረጃ ተጠቅሟል የሚል ክስ አቅርባበታለች። ይህ ሪፖርት በተከከበችው ጋዛ ስላለው ከባድ ሰብአዊ ቀውስ በተከታታይ ማስጠንቀቂያ የሰጡትን የእርዳታ ድርጅቶች እና አለምአቀፍ አካላትን ተከትሎ የወጣ ነው።
"ሂውማን ራይትስዎች አስገድዶ ማፈናቀል በስፋት መፈጸማቸውን፣ ስልታዊ እና የመንግስት ፖሊሲ አካል መሆኑን አረጋግጧል። ይህ ድርጊት በሰብአዊነት ላይ የሚፈጸም ወንጀል ነው" ብሏል ሪፓርቱ።
የእስራኤል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ኦሬን ማርሞርቲን የእስራኤል ጥረት "ንጹሀንን እንደሰብአዊ ጋሻ እንደሚጠቀመው ሀማስ ሳይሆን የሀማስን ሽብር የመፈጸም አቅም የማድቀቅ እንጂ የጋዛን ህዝብ ኢላማ ያደረገ አይደለም።"
ቃል አቀባዩ በመግለጫው "እስራኤል የሁሉንም ንጹሃን ሞት በሀዘን የምታየው ሲሆን ሀማስ ግን እንደስትራቴጂ ነው የሚያየው። እስራኤል የጦርነት ህግን አክብራ ዘመቻዋን ትቀጥላለች" ብለዋል።
ሀማስ ንጹሃንን እንደሰብአዊ ጋሻ መጠቀሙን እና ተዋጊዎቹን እና መሳሪያዎቹን እንደትምህርት ቤት እና ሆስፒታል ባሉ ተቋማት ውስጥ መደበቁን ያስተባብላል። የጦርነት ህግ ንጹሃን ደህንነታቸው አደጋ ውስጥ ካልወደቀ በስተቀር በግዳጅ እንዳይፈናቀሉ ይከለክላል።
እስራኤል በጋዛ ላይ ወረራ የፈጸመችው ሀማስ ባልተጠቀ ሁኔታ ድንበሯን በመጣስ 1200 ሰዎችን ገድሎ ሌሎች 250 ሰዎች አግቶ መውሰዱን ተከትሎ ነበር። ከእዚያ ጊዜ ጀምሮ እስራኤል በጋዛ በወሰደችው መጠነሰፊ ጥቃት ከ43ሺ በላይ ፍልስጤማውያን ሲገደሉ 2.3 ህዝብ ደግሞ ለበርካታ ጊዜ ከቦታ ቦታ እንዲዘዋወር ተገዷል።
ሂውማን ራይትስዎች የፍልስጤማውያን ማፈናቀል ቋሚ መሆኑን እና ከዘር ማጽዳት ወንጀል ጋር እንደሚስተካከል ገልጿል። እስራኤል ጦር ቋሚ የሆነ በፈር ዞን ወይም ከጦር ነጻ ቀጣና ለመፍጠር መፈለጉን ሲያስተባብል የእስራኤል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ሳኣር ተፈናቃዮች ከጦርነቱ በኋላ ወደ ቤታቸው ይመለሳሉ ብለዋል።እስራኤል በምላሹ ተቋሙ "ፍጹም ውሸት እና ከእውነት የራቀ" መረጃ ተጠቅሟል የሚል ክስ አቅርባበታለች