አምስት ሚሊዮን ዩሮ ከአሰሪዋ የተሰጣት እድለኛዋ ሞግዚት
ውርሱ ይደርሰናል በሚል የሟችን መጨረሻ ሲጠብቁ የነበሩ ቤተሰቦች ደንግጠዋል ተብሏል
የ80 አመቷ አዛውንት ያላትን ገንዘብ ሁሉ ለዓመታት ስትንከባከባት ለቆየችው ሞግዚት አውርሳለች
አምስት ሚሊዮን ዩሮ ከአሰሪዋ የተሰጣት እድለኛዋ ሞግዚት
ማሪያ ማልፋቲ የተሰኘች የ80 ዓመት አዛውንት በጣልያኗ ትሬንቶ ግዛት በምትገኘው ሮቬርቶ ከተማ ነዋሪ ነበረች፡፡
የቀድሞ ቬና ምክር ቤት አባል የሆችው እኝህ አዛውንት ልጅም ሆነ ትዳር አልነበራቸውም፡፡ እድሜያቸው እየገፋ ሲመጣም አዛውንቷ ስምንት እህት እና ወንድም ልጆች ንብረታቸውን እንደሚወርሱ እርግጠኞች ነበሩ፡፡
አክስታቸውን ሳይንከባከቡ ንብረታቸውን ብቻ ሲያዩ የቆዩት እነዚህ ሰዎች በመጨረሻም በእርጅና ምክንት ህይወታቸው ያለፈችውን አክስታቸውን ንብረት ለመውረስ ቢሞክሩም አልተሳካም፡፡
የጣልያን ጠቅላይ ሚኒስትር በሩሲያ ድምጽ አስመሳዮች መታለላቸው ተገለጸ
እኝህ አዛውንት ህይወታቸው ከማለፉ በፊት ለረጅም ዓመታ ስትንከባከባቸው ለነበረችው አልባኒያዊት ሞግዚታቸው 5 ነጥብ 4 ሚሊዮን ዶላር ዋጋ ያላቸውን ንብረቶች እና በባንክ የሚገኝ ገንዘባቸውን አውርሰዋል፡፡
አዛውንቷ ሲያመኝ እ ሰው ሲያስፈልገኝ የጠየቀኝ ሰው የለም፣ ዘመዶቼ ይልቅ ሞግዚቴ ብዙ ነገሮችን አድርጋልኛለች ንብረተንም ለዚች ሰው አውርሻለሁ ሲሉ አስቀድመው መጨረሳቸውን ኦዲቲ ሴንትራል ዘግቧል፡፡
የአክስታቸውን ንብረት ለመውረስ አስበው የነበሩት ዘመዶቿም በውሳኔው መደንገጣቸውን እና ያልጠበቁት እንደገጠማቸው በዘገባው ላይ ተጠቅሷል፡፡
እነዚህ የሟች ዘመዶችም ሞግዚቷ የአክስታቸውን መጃጀት በመጠቀም ንብረቶቿን ሁሉ እንዲያወርሷት ሳታደርግ እንዳልቀረች ጥርጣሬ እንዳላቸው ተናግረዋል፡፡