የቀድሞዉ ጠቅለይ ሚኒስትር አብዱልመጀድ ተቦኔ ምረጫውን አሸነፉ
የቀድሞዉ ጠቅለይ ሚኒስትር አብዱልመጀድ ተቦኔ በባለስልጣናት ዘንድ ለወራት የዘለቀዉን ብጥብጥ ያቆማል ተብሎ የታመነበትን ምርጫ ቢያሸንፉም፣ ተቃዋሚዎች የተቃዎሞ እንቅስቃሴያቸውን እንደማያቆሙ ዝተዋል፡፡
ታቃዋሚዎቹ ከአብዱልመጀድ በፊት የነበሩትን አብዱላዚዝ ቦተፍሊካን ከስልጣን ማስወገዳቸዉ የሚታወስ ነው፡፡ በአብዱላዚዝ ቦተፍሊካ ጊዜ በሀዉሲንግ ሚኒስትርነት እንዲሁም ለአጭር ጊዜ ደግሞ በጠቅላይ ሚኒስትርነት ያገለገሉት ተቦኔ ከግማሽ በላይ ድምፅ በማግኘት አሸናፊ ሆነዋል፡፡
ተቦኔ ምርጫውን ከግማሽ በላይ በማሸነፋቸዉ የሁለተኛ ዙር ምርጫ አያስፈልግም ተብሏል፡፡
የሀገሪቱ ባለስልጣናት እንደገለጹት 40 ፐርሰንት መራጮች ተሳትፎ መመዝገቡን ተናረዋል፡፡ ነገር ግን ታቃዋሚዎች በህግ ማዕቀብ የተጣለባቸው እጩዎች መሳተፋቸው ነውር ነው፣ አላማውም አሮጌዎቹን የገዥ መደቦች ቤተ-መንግሰት ለማስቀመጥ ነው ብለዋል፡፡ በሽዎች የሚቀጠሩ ሰልፈኖች አደባበይ ወጥተው ተቃውሞ ያሰማሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡
የቦተፍሊካ የ20 አመታት አገዛዝ ከተወገደ በኃላ የሀገሪቱ ባለስልጣናት ጦሩን ጨምሮ ሀገሪቱን ወደፊት ለማራመድ ብቸኛ አማራጭ ሲያስቀምጡት የነበረዉ ቦተፍሊካ የሚተካ መሪ መምረጥ ነበር፡፡
ነገር ግን ቦተፍሊካን ያስወገደዉ ተቃውሞ በዚያ አላበቃም፣ ይልቁንም ሁሉም የገዥው መደብ አባላት ከስልጣን ገሸሽ እንዲሉ በመፈለግ ተቃውሞው ቀጥሏል፡፡ ራሳቸውን ሂራቅ ብለዉ የሚጠሩት ወጣቶች ስልጣን በአዲስ ጀነሬሽን እንዲተካ ይፈልጋሉ፡፡
“ቦተፍሊካን አስወግደነዋል፤ ሁሉንም የስርአቱን ሰዎችም እናስወግዳልን፤ ተስፋም አንቆርጥም” ሲል ሬይድ መቅረሲ የተባለ የ24 አመት ለሮይተርስ ተናግሯል፡፡ በትናንትናዉ ምርጫ 9 ሚሊዮን መራጮች መሳተፋቹውን የሀገሪቱ የምርጫ በለስልጣናት ተናግረዋል፡፡