በተያዘዉ በጀት ዓመት ኢትዮጵያ ከወጪ ንግድ 916.21 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ገቢ ማግነቷ ተገለጸ
በ2012 በጀት ዓመት አራት ወራት ከግብርና፣ ከማኑፋክቸሪንግ እና ከማዕድን ምርቶች ዘርፍ 1.07 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ገቢ ለማግኘት ታቅዶ የነበረ ሲሆን፡ በአፈፃፀም የተመዘገበው 916.21 ሚሊዮን ዶላር መሆኑን የንግድና ኢነደስትሪ ሚኒሰቴር በድረ ገጹ ይፋ አድርጓል፡፡
ይህ አፈፃፀም ከአምናው በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወራት ከተገኘው 814.73 ሚሊዮን ዶላር ጋር ሲነፃፀር በ 101.48 (12.46 %) ሚሊዮን ዶላር ጭማሪ አሳቷል፡፡
መረጃው እነደሚያመለክተዉ በበጀት ዓመቱ አራት ወራት ከተያዘላቸው ዕቅድ በላይ አፈጻጸም ያስመዘገቡት የወጪ ምርቶች አበባ፣ የአገዳ እህሎች፣ የተፈጥሮ ሙጫና እጣን፣ ጫት፣ እና ኤሌክትሪክ ናቸው፡፡
የዕቅዳቸውን ከ75% እስከ 99% ክንውን ያስመዘገቡ ምርቶች ደግሞ ባህር ዛፍ፣ የጥራጥሬ ሰብሎች፣ ጨርቃጨርቅና አልባሳት፣ ሰም፣ ቡና፣ ታንታለም እና የቅባት እህሎች ናቸው፡፡
በሌላ በኩል ከተያዘው ዕቅድ አንጻር በውጭ ምንዛሪ ገቢ ከ50 በመቶ በታች ዝቅተኛ ገቢ ያስመዘገቡ የወጪ ንግድ ምርቶች እንደቅደም ተከተላቸው ምግብ መጠጥና ፋርማሲቲካልስ፣ ማር፣ የኬሚካልና የኮንስትራክሽን ግብዓት፣ ቅመማ ቅመም፣ ሌሎች ማዕድናት፣ ዓሳ፣ የሥጋ ተረፈ ምርት፣ ወርቅ እና ብረታ ብረት ናቸው፡፡