የትራፊክ አደጋ ተጎጂዎች ተገቢዉን አስቸክዋይ የህክምና አገልግሎት እያገኙ አይደለም በኢትዮጵያ
በኢትዮጵያ ካሉት ከ4 ሺህ በላይ የህክምና ተቋማት ውስጥ አስቸኳይ ህክምና አገልግሎቱን እየሰጡ ያሉት ሁለት ነጥብ ስድስት በመቶ እንደማይበልጡ የመድን ፈንድ አስተዳደር ኤጀንሲ አስታወቀ።
የትራፍክ አደጋ ተጎጂዎች አስቸኳይ የህክምና አገልግሎት ከግልም ሆነ ከመንግሥት ጤና ተቋማት ያለምንም ቅድመ ሁኔታ በነፃ እንዲያገኙ መንግሥት በአዋጅ የደነገገ ቢሆነመ ተጎጅዎች ነፃ የሆነው አስቸኳይ የህክምና አገልግሎት በተገቢው እያገኙ አለመሆኑን የመድን ፈንድ አስተዳደር ኤጀንሲ አስታዉቋል።
የኤጀንሲው ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ሽመልስ ታምራት እንደገለጹት ኤጀንሲው የአስችኳይ ህክምና አገልግሎት አሰጣጥ መመሪያ በማውጣት ለህክምና ተቋማት ያሰራጨ ቢሆንም በዚህ መሰረት አገልግሎቱን እየሰጡ ያሉት አነስተኛ ናቸው።
የተዘረጋው የአሠራር ስርዓት በጤና ሚኒስቴርና በተዋረድ የዘርፉ መስሪያ ቤቶች ግልጽነትና ተጠያቂነትን በሚያስከትል መልኩ እየተሰራ አይደለም።
ኤጀንሲው ቁጥጥር ካደረገባቸው ክልሎች ውስጥ ኦሮሚያ፣ትግራይና አማራ ክልልች የሚገኙ አብዛኛው የግል ሆስፒታሎች የአስቸኳይ ህክምን አገልግሎት እንዳልጀመሩ ማረጋገጣቸውን አቶ ሽመልስ ጠቅሰዋል።
በተለይ የግል ህክምና ተቋማት ከ2 ሺህ ብር በላይ የሚበልጥ ጉዳት የደረሰበትን ተጎጂ ምንም ዓይነት እርዳታ ሳይሰጡ ወደ መንግሥት ሆስፒታል የመላክ ዝንባሌ መኖሩንም አስታውቀዋል።
በጤና ሚኒስቴር የጽኑ ህክምና አገልግሎት ቡድን መሪ አቶ ፍቃዱ ያደታ በበኩላቸው ስራው አዲስ በመሆኑ በሚፈለገው ፍጥነት እየተጓዘ እንዳልሆነ ገልጸው “በቀጣይ አገልግሎቱን በመላ ሃገሪቱ ለማስፋፋት ጥረት ይደረጋል” ብለዋል።
ምንጭ ኢዜአ