የገቢዎች ሚኒስቴር በአንድ ወር ዉስጥ ከ19 ቢሊዮን ብር በላይ ሰበሰበ
የኢትዮጵያ ገቢዎች ሚኒስቴር በህዳር ወር ዉስጥ ብቻ 19 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር መሰብሰቡን አስታውቋል፡፡
የተሰበሰበዉ ገቢ የእቅዱን 104 ፐርሰንት መሆኑንም ገልጿል፡፡
ሚኒስቴሩ በ2011 ዓ.ም. በአገር አቀፍ ደረጃ በተፈጠረዉ ግንዛቤ የግብር ጉዳይ የህዝብ አጀንዳ በመሆኑ ለገቢዉ ማደግ ምክንያት መሆኑን ጠቅሷል፡፡
እንደ ሚኒስቴሩ ገለጻ በህዳር ወር 18.3 ቢሊየን ብር ለመሰብሰብ አቅዶ የነበረ ቢሆንም 19.2 ቢሊየን ብር በመሰብሰብ የእቅዱን 104 በመቶ አሳክቷል ብሏል፡፡
የወሩ ክንዉን ካለፈዉ አመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር በብር የ5 ነጥብ 97 ቢሊየን ብልጫ ያለዉ ሲሆን በፐርሰንትም 36.14 በመቶ እነደሚበልጥ ተነግሯል፡፡