የብሪታንያ ጠቅላላ ምርጫ በኮንሰርቫቲቭ ፓርቲ አሸናፊነት ተጠናቀቀ
በብሪታንያ ጠቅላላ ምርጫ በስልጣን ላይ የሚገኘው ወግ አጥባቂው ኮንሰርቫቲቭ ያገኘው ከፍተኛ ድምጽ ቦሪስ ጆንሰንን በጠቅላይ ሚኒስትርነት ለማስቀጠል የሚያስችል ነው፡፡
ፓርቲው ውጤታቸው ከታወቁት 649 የፓርላማ መቀመጫዎች ውስጥ 76 በመቶ ያህሉን ወይም 364 ድምጽ በማግኘት አሸንፏል፡፡
አብላጫ ድምጽ ያገኘ በሚያሸንፍበት በዚህ የምርጫ ስርዓት ከ650ው የሃገሪቱ ፓርላማ መቀመጫ 326ቱን ያገኘ ነው መንግስት የሚመሰርተው፡፡
የውጤቱ ሁኔታ
ውጤታቸው ከታወቁት 6 መቶ 49 የፓርላማ መቀመጫዎች
ወግ አጥባቂው ኮንሰርቫቲቭ 364
ሌበር 203
ስኮቲሽ ናሽናል 48
ሊብራል ዴሞክራትስ 11
በኒጌል ፋራዥ የሚመራው ብሬግዚት ፓርቲ ደግሞ ምንም ድምጽ ሳያገኝ ቀርቷል፡፡
ቦሪስ ጆንሰን የሚመሩት ወግ አጥባቂው ፓርቲ ማርጋሬት ታቸር ከተሳተፉበት የ1987ቱ ምርጫ ወዲህ በዌስት ሚኒስትር የሚያቆየውን ከፍተኛ ውጤት ነው ያገኘው፡፡
የመሪዎቹ አጸፋ
ውጤቱ ብሬግዚትን በተመለከተ የጀመሩትን የቤት ስራ በማጠናቀቅ በቀጣዩ ወር ዩናይትድ ኪንግደምን ከአውሮፓ ህብረት ለመነጠል እንደሚያስችላቸው ጆንሰን ተናግረዋል፡፡
የመረጡንን ለመካስ ሌት ተቀን እሰራለሁ ብለዋል፡፡
ብሬግዚት ለይደር ሊተው የማይገባ የቀጣይ ወር የቤት ስራቸው መሆኑንም ገልጸዋል፡፡
ፓርቲያቸው ማሸነፉን በገለጹበት የደስታ ንግግርም የቀድሞው የሃገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ቶኒ ብሌር በ1997 የተጠቀሙትን ታዋቂ ንግግር በመጠቀም የሃገሪቱ 'አዲሱ ምዕራዕፍ' ተከፍቷል ብለዋል፡፡
ባልተጠበቀ ሁኔታ ፓርቲያቸውን ደግፈው ድምጽ የሰጧቸውን የሌበር ፓርቲ ደጋፊዎችንም አመስግነዋል፡፡
‘'አምናችሁ እና ተስፋ አድርጋችሁ ለሰጣችሁኝ ድጋፍ በታማኝነት ሌት ተቀን ፍላጎታችሁን ለማሟት በመስራት እክሳችኋለሁ'’ ሲሉም ነው የተናገሩት፡፡
ለጄሬሚ ኮርቢን ግን የምርጫ ምሽቱ የሚያበሳጭ ሆኖ ነው ያለፈው፡፡ ፓርቲያቸው ሌበር ከ1935 ወዲህ ገጥሞት የማያውቀውን ያክል ሽንፈት አስተናግዷል፡፡ እንደሚያሸንፍ ይጠበቅባቸው በነበሩ አካቢዎች እንኳን ሳይቀር ተሸንፏል፡፡
ተስፋን ሊሰጡ የሚችሉ ፕሮግራሞችን ይዘን ብንቀርብም የብሬግዚት ጉዳይ የውጤት ሚዛኑን አዛንፎታል ነው ያሉት ኮርቢን፡፡ በዚህ ምክንያት ማዘናቸውን የገለጹም ሲሆን ከአሁን በኋላ ሌበርን ወክለው በምርጫ እንደማይፎካከሩ ነው የተናገሩት፡፡
የቢቢሲ የፖሊቲካ ጉዳዮች አርታኢ ላውራ ኩንስበርግ የቦሪስን ማሸነፍ ተመሳሳይ ጠቅላይ ሚኒስትር ነገር ግን አዲስ መንገድ ስትል ገልጻዋለች፡፡
ጆንሰን እንደተናገሩት ሁሉ ፓርቲያቸውን መደገፍ እንደሃጢያት ከሚቆጠርባቸው አካባቢዎች ጭምር ድምጽ በማግኘት ለማሸነፍ ችለዋል ብላለች፡፡
በምርጫው ያገኙት ድምጽ የፓርላማ የበላይነትን ከማግኘትም በላይ በየትኛውም በተቃውሞ ጎራ ያለን አካል 'ለማስገበር' የሚያስችል እንደሆነም ነው የጻፈችው፡፡
ምንጭ፡-ቢቢሲ