ፖለቲካ
አብይ አህመድ የብልጽግና ፓርቲ ፕሬዝዳንት ሆነው በድጋሚ መመረጣቸውን ፓርቲው አስታወቀ
ፓርቲው አቶ ተመስገን ጥሩነህ እና አቶ አደም ፋራህን የፓርቲው ምክትል ፕሬዝዳንቶች አድርጎ መምረጡንም ገልጿል
የብልጽግና ፓርቲ 2ኛ መደበኛ ጉባኤ ለሶስት ቀናት ሲካሄድ ቆይቷል
አብይ አህመድ የብልጽግና ፓርቲ ፕሬዝዳንት ሆነው በድጋሚ መመረጣቸውን ፓርቲው አስታወቀ።
2ኛ መደበኛ ጉባኤውን ከጥቅምት 23 2017 ጀምሮ ሲያካሂድ የቆየው የብልጽግና ፓርቲ የፕሬዝዳንት እና ምክትል ፕሬዝዳንቶች ምርጫ አካሂዷል።
በዚህም አብይ አህመድ በድጋሚ የፓርቲው ፕሬዝዳንት ሆነው ተመርጠው በጉባኤተኛው ፊት ቃለ መሀላ መፈጸማቸውን ፓርቲው ባወጣው መግለጫ አመላክቷል።
ጉባኤው አቶ ተመስገን ጥሩነህ እና አቶ አደም ፋራህን የፓርቲው ምክትል ፕሬዝዳንቶች አድርጎ መምረጡም ተገልጿል።
የፓርቲው ፕሬዝዳንት እና ምክትል ፕሬዝዳንቶች ምርጫ ግልጽ በሆነና በዘመናዊ ቴክኖሎጂ መከናወኑንም ነው ብልጽግና ፓርቲ ያስታወቀው።