ትራምፕ በሜክሲኮ፣ ካናዳና ቻይና ላይ ታሪፍ እንዲጣል ትዕዛዝ ሰጡ
ትራምፕ ከቻይና ካናዳ በሚገቡ እቃዎች ላይ የ10 በመቶና ከሜክሲኮ በሚገቡ እቃዎች ላይ ደግሞ የ25 በመቶ ታሪፍ እንዲጣል አስቸኳይ ትዕዛዝ ሰጥዋል
ታሪፎቹ የኑሮ ውድነቱን በማባባስ መራጮች ትራምፕ ቃል መገቡት መሰረት በፍጆታ እቃዎች ላይ የዋጋ ቅናሽ ያደረጋሉ የሚለውን እምነት ሊሸረሽር እንደሚችል ተገልጿል
ትራምፕ በሜክሲኮ፣ ካናዳና ቻይና ላይ ታሪፍ እንዲጣል ትዕዛዝ ሰጥተዋል።
የአሜሪካው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ከካናዳ፣ ሜክሲኮና ቻይና በሚገቡ እቃዎች ላይ ታሪፍ እንዲጣል ትዕዛዝ መስጠታቸው የአሜሪካ ሰሜናዊ ጎረቤት ካናዳ ፈጣን የአጸፋ እርምጃ እንድትወስድና የመከዳት ስሜት እንዲሰማት አድርጓል ተብሏል።
ትራምፕ በካናዳ ላይ ታሪፍ መጣል ከአሜሪካ የረጅም ጊዜ አጋር ጋር የንግድ ጦርነት ጀምረዋል።
የረፐብሊካኑ ፕሬዝደንት ታሪፍ የተጣለው "አሜሪካውያንን ለመከላከል" እና በሶስቱ ሀገራት ህገወጥ የፌንታንይል ምርትና ንግድ እንዲቀንሱ ጫና ለማድረግ እንዲሁም ከካናዳና ሜክሲኮ የሚመጡ ህገወጥ ስደተኞችን ቁጥር ለመቀነስ ያለመ ነው ሲሉ የውሳኔያቸውን ተገቢነት አስረድተዋል።
ታሪፎቹ የሚዘልቁ ከሆነ የኑሮ ውድነቱን በማባባስ መራጮች ትራምፕ ቃል መገቡት መሰረት በፍጆታ እቃዎች ላይ የዋጋ ቅናሽ ያደረጋሉ የሚለውን እምነት ሊሸረሽር እንደሚችል ተገልጿል። ከዚህ በተጨማሪም በሀገራቱ ላይ የተጣሉት ታሪፎች የአለምን ኢኮኖሚና ሁለት ሳምንት የሆነውን የትራምፕን ፖለቲካዊ ስልጣን ቀውስ ውስጥ ሊያስገባው ይችላል የሚል ስጋትም አለ።
ትራምፕ ከቻይና ካናዳ በሚገቡ እቃዎች ላይ የ10 በመቶና ከሜክሲኮ በሚገቡ እቃዎች ላይ ደግሞ የ25 በመቶ ታሪፍ እንዲጣል አስቸኳይ ትዕዛዝ ሰጥዋል።
ነዳጅ ዘይት፣ የተፈጥሮ ጋዝና የኤሌክትሪክ ኃይልን ጨምሮ ከካናዳ የሚገቡ እቃዎች ላይ 10 በመቶ ታሪፍ ይጣልባቸዋል።
"በዛሬው እለት ኃይት ሀውስ የወሰደው እርምጃ አንድ ከማድረግ ይልቅ የሚነጣጥለን ነው" ሲሉ ቅሬታ ያዘለ ንግግር ያሰሙት የካናዳ ጠቅላይ ሚኒስትር ጀስቲን ትሩዶ አልኮል እና ፍራፍሬ ጨምሮ 155 ቢሊዮን ዶላር ዋጋ ባላቸው ወደ ካናዳ በሚገቡ የአሜሪካ እቃዎች ላይ የ25 በመቶ ታሪፍ መጣላቸውን አስታውቀዋል።
ትሩዶ በአፍጋኒስታን ከአሜሪካ ወታሮች ጎን ተሰልፈው የተዋጉትን የካናዳ ወታደሮችንና ከካሊፎርኒያ እስከ ካትሪና የተከሰቱ የተፈጥሮ አደጋዎችን ለመቆጣጠር በሚደረገው ጥረት ካናዳ ያደረገችውን ድጋፍ በማስታወስ ብዙ ካናዳውያን ያሰሙትን የመከዳት ስሜት አንጸባርቀዋል።
ትሩዶ አክለውም "የአሜሪካ ህዝብ ሁል ጊዜ ከእናንተ ጋር እንቆማለን፣ አብረን እናዝናለን" ብለዋል።
የሜክሲኮ ፕሬዝደንት የአጸፋ ታሪፍ እንዲጣል አዘዋል። ቻይና በትራምፕ እርምጃ ላይ ወዲያውኑ ምላሽ አልሰጠችም።
"የሜክሲኮ መንግስት የወንጀለኛ ድርጅቶች ጋር ግንኙነት አለው የሚለውን ስም ማጥፋትና በግዛታችን ላይ ጣልቃ ለመግባት የሚደረገውን ማንኛውንም ፍላጎት በጥቅ እናወግዛለን" ሲሉ የሜክሲኮ ፕሬዝደንት ክላውዲ ሸንባውም በእክስ ገጻቸው ላይ ጽፈዋል።
ፕሬዝደንቱ የኢኮኖሚ ጸኃፊያቸው የአጸፋ ታሪፍንና ሌሎች የሜክሲኮ ጥቅሞችን የሚያስጠብቁ እርምጃዎችን እንዲወስዱ ማዘዛቸውን ጠቅሰዋል።