በምዕራባውያን የሚደገፉት የቬንዙዌላ ዋነኛ ተቃዋሚ ፓርቲ መሪ ወደ ስፔን ኮበለሉ
ፕሬዝደንት ማዱሮ በፈረንጆቹ ሐምሌ 28 የተካሄደው ምርጫ አሸናፊ መሆናቸው ከታወጀ በኋላ ሀገሪቱ ፖለቲካዊ ቀውስ ውስጥ ገብታለች
የተቃዋሚ ፕሬዝደንታዊ እጩ የሆኑት ኢድሙንዶ ጎንዛሌዝ ወደ ስፔን መኮብለላቸውን የቬንዙዌላ መንግስት አስታውቋል
በምዕራባውያን የሚደገፉት የቬንዙዌላ ዋነኛ ተቃዋሚ ፓርቲ መሪ ወደ ስፔን ኮበለሉ።
የተቃዋሚ ፕሬዝደንታዊ እጩ የሆኑት ኢድሙንዶ ጎንዛሌዝ ወደ ስፔን መኮብለላቸውን የቬንዙዌላ መንግስት አስታውቋል።
መንግስት የሚቆጣጠረው ብሔራዊ የምርጫ ኮሚሽን ባለፈው ሐምሌ ወር የተካሄደውን ምርጫ ኒኮላስ ማዱሮ ማሸነፋቸውን ካወጀ በኋላ ጎንዛሌዝ ተደብቀው መቆየታቸውን እና የእስር መያዣም ወጥቶባቸው እንደነበር ቢቢሲ ዘግቧል።
የቬንዙዌላ ምክትል ፕሬዝደንት ዴሊሲ ሮድሪጉዝ በማህበራዊ ገጻቸው ጎንዛሌዝ በካራካስ የሚገኘው የስፔን ኢምባሲ እንዲያስጠልላቸው መጠየቃቸዉን እና ከስፔን መንግስት ጥገኝነት መጠየቃቸውን ገልጸዋል።
ምክትል ፕሬዝደንቷ አክለው እንደገለጹት ካራካስ በሰላም እንዲሄዱ ፈቅዳ ጎንዛሌዝ ከሀገር ወጥተዋል። የስፔን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጆሴ ማኑኤል አልባሬዝ ጎንዛሌዝ በራሳቸው ፍቃድ በስፔን የአየር ኃይል አውሮፕላን ከሀገር ውጥተዋል ብለዋል። የስፔን መንግስት የሁሉንም የቬንዙዌላ ዜጎች የፖለቲካ መብት ለመጠበቅ ቁርጠኛ ነው ብለዋል ምክትል ፕሬዝደንቷ። የስፔን ሚዲያዎች እንደዘገቡት ከሆነ ጎንዛሌዝ በስፔን የፖለቲካ ጥገኝነት አግኝተዋል።
ጎንዛሌዝ ከሀገር እየወጡ ባሉበት ወቅት የጸጥታ ኃይሎች በካራካስ የሚገኘውን የአርጀንቲናን ኢምባሲ ከበው ነበር። ስድስት የፕሬዝደንት ማዱሮ ተቃዋሚዎች በዚህ ኢምባሲ ውስጥ ይገኛሉ።
ፕሬዝደንት ማዱሮ በፈረንጆቹ ሐምሌ 28 የተካሄደው ምርጫ አሸናፊ መሆናቸው ከታወጀ በኋላ ሀገሪቱ ፖለቲካዊ ቀውስ ውስጥ ገብታለች።
አሜሪካን፣ የአውሮፓ ህብረትን እና በርካታ የላቲን አሜሪካ ሀገራትን ጨምሮ ብዙ ሀገራት ካራካስ የምርጫውን መረጃ ይፋ ካላደረገች የፕሬዝደንት ማዱሮን ማሸነፍ አንቀበልም ሲሉ መቃወማቸው ይታወሳል። የማዱሮ መንግስት ከምርጫ ወዲህ ተመድ "የፍርሀት ድባብ መፍጠር" ባለው እርምጃ 2400 ሰዎች ታስረዋል።
ተቃዋሚዎች ማዱሮ 52 በመቶ ድምጽ አሸንፈዋል ያለውን የምርጫ ካውንስል ውጤት አልተቀበሉትም።ጎንዛሌዝም በቁጥጥር ስር ብለው ስለሰጉ ከምርጫው ወዲህ ተደብቀው ቆይተዋል።