የአቡዳቢ አልጋወራሽ አዲስ አበባ ገቡ
ሼክ ካሊድ ቢን መሃመድ ቢን ዛይድ ቦሌ አለማቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ አቀባበል አድርገውላቸዋል
አልጋወራሹ በኢትዮጵያ ቆይታቸው ረሀብን ከአለም የማጥፋት ግብ ባለው ጉባኤ ላይ ይሳተፋሉ
የአቡዳቢ አልጋወራሽ ሼክ ካሊድ ቢን መሃመድ ቢን ዛይድ ማምሻውን አዲስ አበባ ገብተዋል።
አልጋወራሹ ቦሌ አለማቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል።
አልጋወራሽ ሼክ ካሊድ ቢን መሃመድ ቢን ዛይድ እና ወደ ኢትዮጵያ ከእርሳቸው ጋር የመጣው ልኡክ በቦሌ አለማቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ጋር አጭር ምክክር አድርገዋል።
በዚህ ምክክርም የአረብ ኤምሬትስ እና ኢትዮጵያን ትብብር ለማሳደግ በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ውይይት ተደርጓል።
በውይይቱ የሀገራቱን የሁለትዮሽ ጥቅም በሚያሳድግ መልኩ የትብብር ዘርፎቹን ለማስፋት መግባባት መግባባት ላይ ተደርሷል።
በአቡዳቢ አልጋወራሽ የተመራው የኤምሬትስ ልኡክ በአዲስ አበባ ቆይታው ረሃብን ከአለም የማጥፋት ግብ ባለው ጉባኤ ላይ ይሳተፋል ተብሏል።